በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምሥራቅ ሲዳማ ዞን የጭሬ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች አላቂ የቢሮ ዕቃ /እስቴሽነሪ/ ህጋዊ ተጫራቾን አወዳድሮ ዕቃ መግዛት ይፈልጋል።
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የጭሬ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምሥራቅ ሲዳማ ዞን የጭሬ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች አላቂ የቢሮ ዕቃ /እስቴሽነሪ/ ህጋዊ ተጫራቾን አወዳድሮ ዕቃ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች በሙሉ እንዲሳተፉ እንጋብዛለን፡፡
- በዘርፉ ቀጥተኛ የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና ፈቃዳቸው በበጀት ዓመቱ ያሳደሱ፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዘጋቢ የሆኑና ወርሃዊ /VAT/ ሪፖርት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ለአቅራቢነት የተመዘገቡና የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 10,000 /አስር ሺህ/ ብር የጭሬ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ስም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ በማሰራት ማስገባት የሚችሉ፤
- አሸናፊ የሆኑ ድርጅት በቂ ዋስትና ማቅረብ የሚችሉ፤
- በገባው ውል መሠረት ጥራቱንና ደረጃውን የጠበቀ ዕቃ ማቅረብና ቅድመ ናሙና ማሳየት የሚችል ተጫራች ለጨረታ የተዘጋጀው ሰነድ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምስራቅ ሲዳማ ዞን ጭሬ ወረዳ ገቢዎች ባለስልጣን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ውስጥ ጨረታ ሰነድ ከያዘው ባለሙያ እጅ ሰነዱን ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ሰነዱ በመወሰድ ይችላሉ፤ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 14 ቀናት በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እያሳወቅን በ15ኛው ቀን በ6፡00 ሰዓት ታሽጎ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ኦሪጅናል እና ፎቶ ኮፒ ላይ ህጋዊ ማህተም በሰም የታሸገ ፖስታ እንድታስገቡ እናሳስባለን፡፡
- አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበት ዕቃዎች በትክክል የጥራት ደረጃ የጠበቀ ዕቃ በማቅረብ ሲዳማ ብሔራዊ ክልል መንግስት ምስ/ሲ/ዞ/ጭ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ድረስ ማስረከባቸው እንደተረጋገጠ ክፍያው ወዲያ ይፈጽማል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታውን የሚከፈትበትን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- 09-10-74-06-70/09-89-92-55-80/09-26-06-45-20 ደውለው ይጠይቁ፡፡
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የጭሬ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
