Tender Detail

Tender Details


በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በጋሞ ዞን ጤና መምሪያ የአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች እና አገልግሎቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በጋሞ ዞን ጤና መምሪያ የአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል 2018 በጀት ዓመት ለተኝቶ ታካሚ ህሙማንና ለሆስፒታሉ ሠራተኞች አገልግሎት የሚውል

  1. የበሰለ ምግብ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በየስድስት ወሩ የጥራት ሁኔታው ተረጋግጦ ውል እየታደ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ የፈዴራል ጤና ሚኒስቴር ባወጣው የሆስፒታሎች ሪፎርም መሠረት ምና-ነክ ያልሆኑ አገልግሎቶች በኮንትራት/በውል ለሶስተኛ ወገን የተላለፈ ምና-ነክ ያልሆነ አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራትና ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
  2. የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎች
  3. የተለያዩ የንፅህና መገልገያ ዕቃዎች
  4. የተለያዩ የዉሃ የቧንቧ ዕቃዎች
  5. የተለያዩ የኤሌክትሮኒ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድለማሰራት እና ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
  6. ስለዚህ በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፁው መስፈርት መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ
  7. ተጫራቾች በዘርፉ አግባብና ህጋዊ የሆነ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ኦሪጅናል እና ኮፒ፤ የመንግስት አገልግሎት ግዥ በአቅራቢነት ለመሳተፍ የሚያስችል የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ኦሪጅናልና ኮፒ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ክፍያ የምስ ወረቀት /Tin Number/ ኦሪጅናል እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ ካሽጉ በኋላ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ከመጫረቻ ነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. እያንዳንዳቸው ተጫራቾች የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ብር 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር/ ብቻ በባንክ በተረጋገጠ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ገቢ ደረሰኝ /RV/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው
  9. የተጫራቾች የካፒታል መጠን ቢያንስ 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ ብቻ በባንክ ስለመኖሩ የባንክ ስቴትመንት መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  10. ተጫራቾች የሚወዳድሩበት ዋጋ በዋጋ ማቅረቢያው ላይ በጥንቃቄ በመሙላት በእያንዳንዱ ገፅ ፊርማና የድርጅቱን ማህተም በማኖር ዋናውን ሰነድ በአግባቡ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ የድርጅቱን ስምና አድራሻ በግልጽ ኤንቨሎፑ ላይ በመፃፍ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋልተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ታክስን /VAT/ የሚያካትት መሆን አለበት፡፡
  11. የጨረታው ዶክመንት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ በመደበኛ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 300 /ሦስት መቶ ብር/ ሆስፒታላችን ግዥ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብና በመፈል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይቻላል፡፡
  12. የምግብ አቅራቢ ተጫራ ለሥራው የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን በግላቸው ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው
  13. የጨረታው ዶክመንት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አድራሻ በመፃፍ ሕጋዊ የጨረታ ማስታውቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን
  • ከላይ ለተዘረዘሩት ለተራ ቁጥር 1. 16ኛው የሥራ ቀን
  • ከላይ ለተዘረዘሩት ለተራ ቁጥር 2. 17ኛው የሥራ ቀን
  • ከላይ ለተዘረዘሩት ለተራ ቁጥር 3. 18ኛው የሥራ ቀን
  • ከላይ ለተዘረዘሩት ለተራ ቁጥር 4. 19ኛው የሥራ ቀን
  • ከላይ ለተዘረዘሩት ለተራ ቁጥር 5. 20ኛው የሥራ ቀን፡ ከጠዋት 300-400 ሰዓት ባለው  በሆስፒታላችን ግዥ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል ለዚህ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የመጫረቻ ፖስታ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  1. ጨረታውን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ቦታ ማለትም
  • ከላይ ለተዘረዘሩት -
  • ለተራ ቁጥር 1. 16ኛው የሥራ ቀን
  • ለተራ ቁጥር 2. 17ኛው የሥራ ቀን
  • ለተራ ቁጥር 3. 18ኛው የሥራ ቀን
  • ለተራ ቁጥር 4. 19ኛው የሥራ ቀን
  • ለተራ ቁጥር 5. 20ኛው የሥራ ቀን፡ ከቀኑ 900 ሰዓት ላይ የታሸገው የጨረታ ሳጥን ይከፈታል፡፡
  1. ተጫራቾች በጨረታ ፈቻ ሰዓት ያለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም፡፡
  2. ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

ለተጨማሪ ማብራራያ በስልክ ቁጥር፡- 09-11-58-92-26/09-10-03-51-29 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

 

በጋሞ ዞን ጤና መምሪያ የአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል

 

Save Tender