Tender Detail

Tender Details

  • Company በስልጤ ልማት ማህበር የሀይረንዚ ልዩ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Address ደቡብ ክልል ኢትዮጵያ, Phone: 0467710462
  • Website
  • Deadline25 Sep 2026, 3:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price
  • opening dateበዚሁ ዕለት 9፡30
  • Categories Food And Beverage , Consumable Goods , Food Items And Drinks

በስልጤ ልማት ማህበር (ስልማ) የሀይረንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2019 የት/ት ዘመን ለሚያስተምራቸው እስከ 480 ለሚደርሱ ተማሪዎች ቀለብ አገልግሎት የሚውል የባልትና ዕቃዎች ጥራጥሬ፣ የምግብ ሸቀጣሸቀጥ፣ ዳቦ፣ የጤፍ ዱቄት የማገዶ እንጨት እና ስጋ በጨረታ አወዳድሮ ከአቅራቢዎች መግዛት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

በስልጤ ልማት ማህበር (ስልማ) የሀይረንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2019 የት/ት ዘመን ለሚያስተምራቸው እስከ 480 ለሚደርሱ ተማሪዎች ቀለብ አገልግሎት የሚውል የባልትና ዕቃዎች ጥራጥሬ፣ የምግብ ሸቀጣሸቀጥ፣ ዳቦ፣ የጤፍ ዱቄት የማገዶ እንጨት እና ስጋ በጨረታ አወዳድሮ ከአቅራቢዎች መግዛት ይፈልጋል፡፡

የዕቃዎቹ ዝርዝር

የሚያስይዙት የጨረታ ማስከበሪያ CPO መጠን
1. ሰጥራጥሬ፣ የምግብ ሸቀጣሸቀጥ ዘይት፣ ስኳር እና የባልትና ዕቃዎች ------ ብር 5000.00
2. ለዳቦ ------ ብር 2000.00
3. ለጤፍ ዱቄት ------ ብር 5000.00
4. ጥሬ ስጋ ------ ብር 3000.00
5. ለመገዶ እንጨት ------ ብር 3000.00

በጨረታው ስመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው፡-

  1. በዘርፉ ሕጋዊ የሥራ ፍቃድና የሥራ ልምድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን የሥራ ግብር ከፍለው ያጠናቀቁ፡፡
  3. የቲን ቁጥር ያላቸው ስለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  4. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ CPO በሚወዳደሩበት ዕቃ በተጠየቀው መጠን ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. አሸናፊ የሆነ ድርጅት ንብረቱን እስከ ሀይረንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በውሉ መሰረት ማቅረብ የሚችል፡፡
  7. ጨረታውን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ለመወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች የጨረታ ሰነዱን ከሀይረንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  8. ከአንድ በላይ በሆኑ ዕቃዎች የሚወዳደር እቅራቢ በእያንዳንዱ በሚወዳደርባቸው ዕቃዎች የተጠየቀውን CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  9. ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ15ኛው ቀን ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 9፡30 በሀይረንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በሳምንት መጨረሻ ቀናት ወይንም የበአል ቀናት ላይ ካረፈ የጨረታው መዝጊያ እና መከፈቻ ቀን ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡
  10. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ሰነድ በሰም የታሸገ ፖስታ ሆኖ ስማቸውን ፤ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
  11. የሚቀርበው ሰነድ በዋና እና በኮፒ መሆን ይኖርበታል፡፡
  12. ስርዝ ድልዝ ያለው ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  13. ተጫራቾች ሆኑ ወኪሎቻቸው ጨረታው ሲከፈት ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት የሚያስቀረው ነገር ሊኖርአይችልም፡፡
  14. ት/ቤቱ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. አሸናፊ የሚሆነ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች አሸናፊነታቸው ከተገለጸበት ጊዜ አንስቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ማቅረብ መጀመር የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

ለበስጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0467710462 ደውስ መጠየቅ ይቻላል፡፡

በስልጤ ልማት ማህበር የሀይረንዚ ልዩ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

✨ messages.ai_summary
Silte Development Association's Hayrenzi Special Secondary School seeks suppliers for food and related goods for up to 480 students: pulses, food items, bread, teff flour, firewood, and meat. Bidders must have a valid license, experience, tax clearance, TIN, VAT registration, and a CPO.
Save Tender