Tender Detail

Tender Details


የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የደንብ ልብስ፣የዶሮና እንቁላል፤ የታሸጉ ምግቦች፤የጥራጥሬ እና የስጋ ግብአቶችን ግዢ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡


                                                                             የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 001/18

የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የደንብ ልብስ፣የዶሮና እንቁላል፤ የታሸጉ ምግቦች፤የጥራጥሬ እና የስጋ ግብአቶችን ግዢ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ስለሆነም የሚወዳደሩ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡በዚህም መሰረት፡- ለግብር ዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታከስ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ ክሊራንስ ወይም በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ተፈላጊ ሰነዶች ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡ ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለı5 ተከታታይ ቀን ሲሆን ሰነድ የሚሸጠው በስራ ሰአት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00 ሰዓት እስከ 1፡00 ሰዓት የማይመለስ 100 /አንድ መቶ ብር/ አዲስ አባባ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 207 ሽያጭ ከፍል በመክፈል ደረሰኝ ይዘው ቢሮ ቁጥር 208 አቅርቦትና ኮንትራት አስተዳደር ቡድን ቢሮ በመምጣት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ ፡፡የጨረታ ፖስታውን ፋይናንሻል እና ቅድመ መገምገሚያዎችን /ቴክኒካል ሰነድ/ በተለያየ ፖስታ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት አሽጎ ማቅረብ አለባቸው፡፡ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን የጨረታ ሰነድ ላይ/ የተገለፀውን ብር በሲፒኦ ወይም በባንክ ዋስትና ከቴክኒካል /ህጋዊ ሰነዶች/ ኦርጅናል ሰነድ ጋር ወይም ለብቻው በፖስታ አሽጎ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለı5 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀን አየር ላይ ይውልና በ15ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከ8፡30 ጀምሮ ተጨራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል ። ኢንስቲትዩቱ ጨረታውን እንዳስፈላጊነቱ በከፊል ወይም በሙሉ የመስረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

አአድራሻ፡- አዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ስልክ ቁጥር 0116-454147/0116-453598 /0118-694931 ከሳሊህተ ምህረት ማርያም ቤ/ክርስትያን ፊት ለፊት የሚገኘው ህንፃ

                                                                               የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት

Save Tender