Tender Detail

Tender Details

  • Company የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት መስኖ ተቋማት ልማትና አስተዳደር ኤጄንሲ
  • Address ወልቂጤ ከተማ : በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 251 113658470
  • Website
  • Deadline31 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price150.00
  • Bid Security5,000.00 (አምስት ሺህ ብር)
  • opening date2025-10-31 00:00:00
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment , Stationery Materials

የማ/ኢ/ክ/መንግሥት መስኖ ተቋማት ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት ጥቅል ግዥ ለመግዛት ሎት አላቂ የቢሮ የጽህፈት መሳሪያ ዕቃዎችና አላቂ የቢሮ የጽዳት ዕቃዎች ሕጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት መስኖ ተቋማት ልማትና አስተዳደር ኤጄንሲ


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር:- 002/2018 ዓ.ም

 

የማ/ኢ/ክ/መንግሥት መስኖ ተቋማት ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት ጥቅል ግዥ ለመግዛት ሎት አላቂ የቢሮ የጽህፈት መሳሪያ ዕቃዎችና አላቂ የቢሮ የጽዳት ዕቃዎች ሕጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

  1. ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የ2018 በጀት ዓመት ዕድሳት የፈፀሙ፣ እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
  2. የግብር ከፋይነት /ቲን/ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
  3. የጨረታ አሸናፊ ከሆኑ ከግዥው ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ማስያዝ የሚችሉ፤
  4. ከሚመለከተለው የመንግሥት ተቋም ኦንላይን /Online/ የምዝገባ /የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  5. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን /የሚሞሉት/ የአንዱ ዋጋ 15% ቫትን ያካተተ ወይንም ያላካተተ መሆኑ መገለጽ ይኖርበታል።
  6. ከ50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በላይ የሚጫረቱ ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ፎቶ ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሠረት የሚወዳደሩበትን ዋጋ በመሙላትና በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ፈርማና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋናውን እና አንድ አንድ ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  8. ተጫራቾች ቴክኒካልና ፋይናንሻል 1 ኦሪጅናል እና 1 ኮፒ በማዘጋጀት ማቅረብ አለባቸው።
  9. ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ለተወዳደሩባቸው የጽህፈት መሳሪያዎችና የጽዳት ዕቃዎች ለእያንዳንዳቸው ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ናሙና ያለቀረበባቸው የዕቃ ዓይነቶች ከውድድር ውጪ ይሆናሉ።
  10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒአ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሠረተ የባንክ ጋራንት ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  11. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ ከመስኖ ተቋማት ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ይዘው በመቅረብ የማይመለስ 150 ብር ብቻ በመክፈል በቢሮ ቁጥር 9 ማግኘት ይችላሉ።
  12. ተጫራቾች የዚህን የጨረታ ሰነድ መመሪያ በሚገባ በመረዳት የጨረታ ሰነዳቸውን ሞልተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እሰከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስ/ተቋ/ልማትና አስ/ኤጄንሲ ግዥ/ን/አስ/ዳይ 9 ቁጥር ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
  13. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል። 15ኛው ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል።
  14. ጨረታውን ለማወክ የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ እንደሚሆኑ እና ለወደፊትም በመንግስት ዕቃ/አገልግሎት ግዥ እንዳይሳተፉ እንደሚደረግ እና ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና እንደሚወረስ ማወቅ አለባቸው።
  15. ተጫራቾች ይፋ በሚደረገው ውጤት መሰረት ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች አሸናፊነታቸው ተገልፆ ውል በተፈራረሙ በ15 ቀናት ውስጥ ወልቂጤ በሚገኘው የመስኖ ተቋማት ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ መጋዘን ማስረከብ አለባቸው።
  16. ኤጄንሲው በግዥው ዝርዝር ፍላጎት ላይ 20% የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው።
  17. ኤጀንሲው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር:- +251-1-13-65-84-70

 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት መስኖ ተቋማት ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ

 

Save Tender