በማ/ኢ/ክ/መንግስት የመስኖ ተቋ/ልማ//አስ/ኤጄንሲ በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት ጥቅል ግዥ ለመግዛት ለኤጄንሲው ባለሙያዎችና ሠራተኞች የደንብ ልብስ ሕጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት መስኖ ተቋማት ልማትና አስተዳደር ኤጄንሲ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ግልጽ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 003/2018
በማ/ኢ/ክ/መንግስት የመስኖ ተቋ/ልማ//አስ/ኤጄንሲ በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት ጥቅል ግዥ ለመግዛት ለኤጄንሲው ባለሙያዎችና ሠራተኞች የደንብ ልብስ ሕጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
በመሆኑም፤
- ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የ2018 በጀት ዓመት ዕድሳት የፈፀሙ እንድሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይነት /ቲን/ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ፋይናንስ ማስረጃ መቅረብ የሚችሉ፣
- የጨረታ አሸነፊ ከሆኑ ከግዣው ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም በሁኔታ ለይ ያልተመሰረተ የባንከ ጋራንቲ ማስያዝ የሚችሉ፣
- ከሚመለከተው የመንግሥት ተቋም ኦንላይን /Online/ ሲስተም የምዝገባ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት /የሚሞሉት/ የአንዱ ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን ይኖርበታል፣
- ከ50,000.00 (ሃምሳ ሺ ብር) የሚጨረቱ ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ መያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሠረት የሚወዳደሩበትን ዋጋ በመሙላትና በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ፈርማና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋናውን እና እንድ አንድ ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርበቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ቴክኒካልና ፋይናንሻል 1 ኦርጅናል እና 1 ኮፒ በማዘጋጀት ማቅረብ አለበቸው።
- ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ለተወዳደሩባቸው ለደንብ ልብሶች ጫማዎችና ሸሚዞች ለእያንዳንዳቸው ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ናሙና ያልቀረባበቸው የዕቃ ዓይነቶች ከውድድር ውጪ ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመስከረለት ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሠረተ የባንክ ጋራንቲ ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ ከመስኖ ተቋማት ልማትና አስተዳደር ኤጄንሲ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ይዘው በማቅረብ የማይመለስ 150 ብር ብቻ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የዚህን የጨረታ ሰነድ መመሪያ በሚገባ በመረዳት የጨረታ ሰነዳቸውን ሞልተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ የመስኖ ተቋማት ልማት አስተዳደር ኤጄንሲ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 9 ቁጥር ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ እንዲሆኑ እና ለወደፊትም በመንግስት ዕቃ /አገልግሎት ግዥ እንዳይሳተፉ እንደሚደረግ እና ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና እደሚወረስ ማወቅ አለባቸው።
- ተጫራቾች ይፋ በሚደረገው ውጤት መሰረት ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች አሸናፊነታቻው ተገልፆ ውል በተፈራረሙ በ15 ቀናት ውስጥ ወለቂጤ በሚገኘው የመስኖ ተቋማት ልማትና አስተዳደር ኤጄንሲ መጋዘን ማስረከብ አለባቸው።
- ኤጄንሲው በግዥው ዝርዝር ፍላጎት ላይ 20% የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው።
- ኤጄሲው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 251 113658470
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት መስኖ ተቋማት ልማትና አስተዳደር ኤጄንሲ
ወልቂጤ
