Tender Detail

Tender Details


ኢትዮ ፐልፕ እና ወረቀት አክሲዮን ማህበር በ2018 በጀት ዓ.ም ለፋብሪካ ግብዓት የሚሆኑ የተለያዩ ፓምፖች እና የፋብሪካ ሞተሮች መለዋወጫ ዕቃዎች፤ ለወረቀት ማምረቻ የሚሆኑ ቀለሞች እና ኬሚካሎች፤ ደንብ ልብስ እና የጽዳት ዕቃዎችን ህጋዊ ነጋዴዎችን በየንግድ ዘርፋቸው አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል።

ኢትዮ ፐልፕ እና ወረቀት አክሲዮን ማህበር


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

ኢትዮ ፐልፕ እና ወረቀት አክሲዮን ማህበር በ2018 በጀት ዓ.ም ለፋብሪካ ግብዓት የሚሆኑ የተለያዩ ፓምፖች እና የፋብሪካ ሞተሮች መለዋወጫ ዕቃዎች፤ ለወረቀት ማምረቻ የሚሆኑ ቀለሞች እና ኬሚካሎች፤ ደንብ ልብስ እና የጽዳት ዕቃዎችን ህጋዊ ነጋዴዎችን በየንግድ ዘርፋቸው አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም እጩ ተጫራቾች ቀጥሉ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ሟሟላት ይጠበቅባቸዋል።

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉና ንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ መሆን አለባቸው።
  2. ተጫራቾች የተጨማሪ ታክስ ከፋይ ወይም ቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
  3. የንግድ መለያ ቁጥር (TIN number) ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሠነድ ከነዋጋ ማቅረቢያው በታሸገ ኤንቨሎፕ ኮፒና ኦሪጅናል በመለየት ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረታውም በ16ኛው ቀን ከቀኑ 6፡30 ታሽጎ በዕለቱ በ8፡00 ሰዓት ዋና መሳሪያ ቤት ወንጂ ቢሮ ቁጥር 4 (የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የጨረታ መክፈቻ ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል ፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ) ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ቢድ ቦንድ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ማንኛውም እጩ ተጫራች ያሸነፈበትን ዕቃ ለማቅረብ አስቀድሞ ከድርጅቱ ጋር በአምስት የስራ ቀናት ውል ለመፈረም ፈቃደኛ መሆን አለበት፡፡
  7. ተጫራቾች በፌደራል ወይም በኦሮሚያ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ አቅራቢዎች መዝገብ ላይ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አ/አበባ ሽሮ ሜዳ አሜሪካን ኢንባስ ፊት ለፊት ቢሮ ቁጥር 33 እና ዋና መስሪያ ቤት ወንጂ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ በብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) መግዛት ይችላሉ፡፡
  9. ከቀረበው አጠቃላይ የግዢ ዋጋ ድርጅቱ 50% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. የጠቅላላ የዕቃዎች ግዥ ዋጋ 20,000.00 (ሃያ ሺህ) ብር ከሆነ 3% ተቀናሽ ይሆናል፡፡ (with holding)
  11. ማንኛውም ተጫራች ካሸነፈበት ጠቅላ ዋጋ ላይ 10% በሲፒአ መይም በቼክ የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  12. ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን ካሸነፈ ከድርጅቱ ጋር ውል ከተፈራረመ በኋላ ዕቃውን ወንጂ የሚገኝ ድርጅቱ ጊቢ በራሱ ማጓጓዣ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  13. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል፡፡ ይህም ሲሆን ጨረታው በመሰረዝ ምክንያት ተጫራቾች በጨረታው ለማወዳደር ለወጡት ወጪ አክሲዮን ማህበሩ ኃላፊነት አይወስድም፡፡

 

ለበለጠ መረጃ ሥ.ቁ 022-220-1793

022-220-2118

 

ኢትዮ ፐልፕ እና ወረቀት አክሲዮን ማህበር

 

Save Tender