የመከላከያ ኮንስትራክሸን ኢንተርፕራይዝ የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች፣ ማሽነሪዎች፣ ቀላል የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች (Auxillary Equipments) ፣ ያገለገለ ጎማ እና ባትሪ መነሻ ዋጋ በማስቀመጥ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
Defense Construction Enterprise (የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ)
የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች፣ ማሽነሪዎች፣ ቀላል የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች
(Auxillary Equipment)፣ ያገለገለ ጎማ
እና ባትሪ መነሻ ዋጋ በማስቀመጥ ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የመከላከያ ኮንስትራክሸን ኢንተርፕራይዝ የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች፣ ማሽነሪዎች፣ ቀላል የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች (Auxillary Equipments) ፣ ያገለገለ ጎማ እና ባትሪ መነሻ ዋጋ በማስቀመጥ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በሽያጭ ጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተጫራቾች መስፈርት የማከበርና የመፈፀም ግዴታ አለባቸው።
- ይህ ጨረታ ድርጅት ወይም ግለሰብ ሊሳተፍበት ይችላል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሠነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ሙሉቀን እንዲሁም ቅዳሜ ግማሽ ቀን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሽያጭ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ሙሉቀን እንዲሁም ቅዳሜ ግማሽ ቀን ባሉት የሥራ ቀናት ጠዋት 3፡00 እስከ 6፡00 ከሰዓት ከ7፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ቃሊቲ ግቢ (ቃሊቲ ቶታል አካባቢ በሚገኘው የኢንተርፕራይዙ ግቢ) እና ወርቁ ሰፈር በአካል በመገኘት መመልከት ይችላሉ፡፡
- አንድ ተጫራች የተለያዩ የማሽነሪ፣ ተሸከርካሪዎች፣ ቀላል የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች፣ ያገለገሉ ጎማዎች እና ባትሪዎች ዓይነታቸውን መሰረት በማድረግ የሚገዛበትን የአንድ ዋጋ እና ጠቅላላ የሚገዛውን መጠን በማስገባት መጫረት ይኖርበታል፡፡
- የዚህ ጨረታ ከተቀመጠው መነሻ ዋጋ በታች መጫረት አይቻልም፡፡ ከመነሻ ዋጋ በታች ያስገቡ ተጫራቾች በቀጥታ ከጨረታው ውድቅ ይደረጋሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ ሲገዙ ትክክለኛ አድራሻቸውንና ሥማቸውን በመግለጽ ፈርመው መውሰድ አለባቸው።
- ጨረታው ጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው (በዕለቱ) በ4፡30 (አራት ሰዓት ተኩል) ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ በመቅረታቸው የጨረታውን መከፈት እያስተጓጉልም፡፡
- ኢንተርፕራዙ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ጋር የመታወቂያ እና የጨረታ ሠነድ የገዙበትን ደረሰኝ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ለሽያጭ የቀረቡት የተለያዩ ዓይነት፡-
- ዶዘር
- ሎደር
- ኮንክሪት ሚክሰር
- ዳምፐር
- ጀኔሬተር
- ዌልዲንግ ማሽን
- ወክ ቢሃይንድ ሮለር
- ቀላል ተሽከርካሪ እና ከባድ ተሸከርካሪ
- ያገለገሉ ባትሪዎች እና ጎማዎች
- ቫይብሬተሮች ፣ ታምፐር ኮምፓክተር ፣ ዎተር ፓምፕ እና ከተር
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ቃሊቲ ግቢ ስልክ ቁጥር
011-4-40-34-34
ማዞሪያ 011-4-42-22-70/71/72
E-mail አድራሻ info@dce-et-com
የድረ-ገጽ አድራሻ WWW.dce-et.com
ፖ.ሳ.ቁ. 3414 114-40-40-71/0114-42-07-46
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
