የብርሃን ጉዞ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም የተለያዩ ለትምህርት የሚውል የፅህፈት መሳሪያዎች ፤ ህንፃ መሳሪያ የስፖርት እቃ ፤የደንብ ልብስ፣ ኤሌክትሮኒከስ ፤ የኮምፒዩተር እቃ፤ መጽሐፍትና የቢሮ እቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የብርሃን ጉዞ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001
የብርሃን ጉዞ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም የተለያዩ ለትምህርት የሚውል የፅህፈት መሳሪያዎች ፤ ህንፃ መሳሪያ የስፖርት እቃ ፤የደንብ ልብስ፣ ኤሌክትሮኒከስ ፤ የኮምፒዩተር እቃ፤ መጽሐፍትና የቢሮ እቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ
- በሚወዳደሩበት የስራ ዘርፍ ህጋዊ ፍቃድና የንግድ ምዝገባ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
- የተጨማሪ የእሴት ታከስ ተመዝጋቢ መሆናቸውንና የንግድ ምዝገባ የምስከር ወረቀት ያላቸው
- በኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ አቅራቢነት የተመዘገበና ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ
- የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ በcpo በእያንዳንዱ ሎት ከሚያቀርበው አጠቃላይ ዋጋ ላይ 2% ማቅረብ የሚችል
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በተገለፀ በ7 ቀን ውስጥ ውል መፈፀም እና 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ cpo ማስያዝ የሚችል ::
ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰአት በት/ቤቱ ሂሳብ ከፍል ቢሮ ቁጥር 02 የማይመለስ ብር 300/ ሶስት መቶ ብር /በመከፈል ሳምፕል እቃዎችን ቢሮ ቁጥር 06 ማስገባት ይችላሉ ፡፡
ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በወጣ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት ከጠዋቱ በ 4፡30 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች የተጫረቱበትን ዋጋ ሰነዱ ውስጥ በተዘጋጀው ዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ላይ ብቻ ከነቫቱ በመሙላት የድርጅታቸውን ማህተምና ፊርማ አኑረው ፋይናንሺያል ኮፒና ኦሪጅናል ቴከኒካል ኮፒና ኦሪጅናል ለብቻ ለብቻ በድምሩ 4 ፖስታ ከላይበተጠቀሰው መጨረሻው ቀን ድረስ ዘወትር በስራ ሰአት ከ 2፡30 እስከ 11፡00 በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ጨረታ እቃ /ናሙና/ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡ ያለበለዚያ ከጨረታ ውጪ ናቸው :: ተጫራቾች በተመረጠው ናሙና መሰረት በ7 ቀን ውስጥ እቃዎቹ በት/ቤቱ እቃ ግምጃ ቤት ድረስ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡ ፈርኒቸር ፤ የኤሌክትሮኒከስ እቃዎች፣ ኮምፐዩተሮችና የህንፃ መሳሪያ ናሙና በምስል ማቅረብ ይቻላል፡፡
ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት መወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ አይችሉም፡፡
መ/ቤቱ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብት አለው
አድራሻ ፡- ካዛንቺስ እንደራሴ ከፍ ብሎ ብርሃን ጎዞ እ/ህ/መ/ደ/ት/ቤት
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0118931312/0118932990
የብርሃን ጉዞ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ት/ቤት
