Tender Detail

Tender Details

  • Company Central Ethiopia Transport & Road Development Bureau (የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ)
  • Address ከጉራጌ ዞን አስተዳደር ጎን ፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት : ኢትዮጵያ, Phone: 0113659360
  • Website
  • Deadline27 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security2%
  • opening date2025-10-27 00:00:00
  • Categories Cleaning & Janitorial , Stationery Materials , Office Equipment

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ለ2018 በጀት አመት ለቢሮ ሥራ የሚያገለግል የእስቴሽነሪ እና የጽዳት ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Central Ethiopia Transport & Road Development Bureau (የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ)


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር ትራ/መን/ል/መደ/001/2018

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ለ2018 በጀት አመት ለቢሮ ሥራ የሚያገለግል የእስቴሽነሪ እና የጽዳት ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች

1. የተጨማሪ እሴት ታከስ /NAT/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክርወረቀት ማቅረብ የሚችሉ

2. የዘመኑን ግብር የከፈሉና አግባብ ያለው የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው

3. በፋይናንስ መስሪያ ቤቶች በዕቃ አቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡና በህግ ያልተገደቡ

4. የቲን ተመዝጋቢነት ምስከር ወረቀት ያለዉ

5. ለእያንዳንዱ ዕቃ ግዥ ከቢሮ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት የቢሮ የግዥ/ንብ/ አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡

6. በኦንላይን የተመዘገበ

7. የዕቃውን አይነት ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡

8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ የቴከኒካል የጨረታ ሰነድና የፋይናንስ የጨረታ ሰነድን ለብቻ ለብቻ ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለተዘጋጀ የቴክኒከና የፋይናንስ ሰነድ ተጨማሪ ተመሳሳይ አንድ አንድ ኮፒዎች አዘጋጅተው በየኤንቬሎፕ የውጭ ገጽ ዋና /ኦርጂናል/ወይም/ ኮፒ ብሎ በመፃፍ አሽገው ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

9. በማንኛውም ኤንቬሎፕ ውስጥ የጨረታ ማስከበሪያ ማስገባት የለባቸውም፤ ስለተጫራቾች የንግድ ፈቃድ የቫት ሰነድ መልካም አፈጻጸም ወዘተ መካተት ያለባቸውበቴከኒክ የጨረታ ሰነድ በሆኑት በዋናው ኦሪጅናል እና ev ኮፒ ተብሎ በተገለጹት በሁለቱም ኤንቬሎፕ ሲሆን በፋይናንሻል የጨረታ ሰነድ በዋናው (ኦርጅናል / ሆኖ ኮፒ ኤንቨሎፕ ውስጥ ከፋይናንሻል የጨረታ ሰነድ ውጭ ምንም ተጨማሪ መረጃ ማስገባት አይፈቀድም፤

 

10. ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአየር የሚውል ይሆናል፡፡ ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን የሚያስገቡት በ16ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የቢሮ አድራሻ በግልጽ ፋይናንሻልና ቴከኒካል ሰነድ አንድ ላይ በተጫራች ፊት ተከፍቶ በንባብ ይሰማል ፡፡ ሆኖም 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው የሚዘጋውና የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ይሆናል፡፡ ማንኛውም የተጫራቾች ህጋዊ ወኪል በፍርድ ቤት የተረጋገጠና በኢፌድሪ/ በከልሉ መንግስት ህጐች ተቀባይነት ያለው ኦርጅናል የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት ፎቶ ኮፒ ተደርጐ ብቻ የሚመጣ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡

11. ማንውዉም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት ለሚወዳደሩት ሎት ከጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 2% ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ቼከ ወይም ከታወቀ በባንከ ዋስትና የሚቀርብ በባንክ ዋስትና ለብቻው በታሸገ ፖስታ መሆን አለበት፡፡

12. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ/ጉ አቅራቢ/ዎች /ተጨማሪ መረጃ የሚፈልጉ ከሆነ በቢሮ ስልከ ቁጥር 0113659360 ዘወትር በስራ ሰዓት መጠየቅ ይችላሉ፡፡

13. ቢሮው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

የቢሮ አድራሻ፡- ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ የጉራጌ ዞን አስተዳደር ጎን መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ

Save Tender