Tender Detail

Tender Details

  • Company Debre Birhan Wood Processing Pvt. Ltd (የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር)
  • Address ደብረ ብርሃን ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011637 58 03
  • Website
  • Deadline27 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-10-27 00:00:00
  • Categories Industry And Factory , Byproducts

የደብረ ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማህኅበር በፋብሪካው ግቢ በምርት ሂደት ላይ የሚመረቱ የተለያዩ ተረፈ ምርቶችን በተለያየ ክፍልፋይ (ሎት) ከፋፍሎ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Debre Birhan Wood Processing Pvt. Ltd (የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር)


 

ክፍል 1 ግልፅ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የደብረ ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማህኅበር በፋብሪካው ግቢ በምርት ሂደት ላይ የሚመረቱ የተለያዩ ተረፈ ምርቶችን በተለያየ ክፍልፋይ (ሎት) ከፋፍሎ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች በቀረበው ዝርዝር መረጃ መሠረት መወዳደር የምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን። የተረፈ ምርቶቹን ዓይነት እና ዝርዝር ስፔስፊኬሽን ከጨረታው መመሪያ ሰነድ ማግኘት ይቻላል ወይም በፋብሪካው ቦታ ላይ በአካል በመገኘት ማየት ይቻላል፤

የጨረታ ሰነዱን ከድርጅቱ ፋይናንስ ክፍል የማይመለስ 200 ብር ከፍሎ መግዛት ይቻላል

    1. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት በጨረታው መመሪያ ላይ በተገለፀው የብር መጠን መሠረት በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ በሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው።
    2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ዋጋውን እና አስፈላጊ መረጃዎችን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደ/ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
    3. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ የካላንደር ቀናት አየር ላይ ይሆናል፡፡ ሆኖም ግን ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት 4፡30 ተጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡
    4. የጨረታ መክፈቻው ቀን የበዓል ቀን ወይም እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ወይም በማግስቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
    5. ተጫራቾቹ ከሥራ መስኩ ጋር ተያያዥነት ያለው ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የVAT እና TIN ሰርተፊኬት የማይመለስ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፤ በውክልና የሚወዳደሩ አካላት ከፍትሕ ወይም ከሰነዶች ማረጋገጫ ሕጋዊ የውክልና ሰነድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
    6. መሥሪያ ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

❖ ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0116375803 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

 

ደብረ ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር

 

Save Tender