Tender Detail

Tender Details

  • Company በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251112730852
  • Websitehttps://www.fsc.gov.et/
  • Deadline06 Nov 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየንብረቱን ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O
  • opening dateጥቅምት 27 ቀን 2019 ዓ.ም
  • Categories Land , House, Building And Warehouse , Business, Industry And Factory Foreclosure , Industry And Factory

በደብረብርሃን ከተማ ገንደበል ቡለን ቀበሌ የሚገኝ ዳሺያንግ ማኑፋክቸሪንግ የቀለም ፋብሪካ ከነሙሉ ንብረቶች የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት ብሩክ ቱርጋ እና በፍ/ባለዕዳ እነ ዳሺያንግ ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.22026 በ30/06/2018ዓ.ም እና የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.24141 በቀን 28/08/2018ዓ.ም በዋለው ችሎት በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በፍ/ባለዕዳ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ዳሺያንግ ማኑፋክቸሪንግ የቀለም ፋብሪካ የሚገኝበት አድራሻ በደብረብርሃን ከተማ ልዩ ቦታው ገንደበል ቡለን ቀበሌ የካርታ ቁጥር 1804 የቦታ ስፋት 11,342.36 ካ/ሜ (1.13 ሄ/ር) ሎት ያረፈ የቀለም ፋብሪካ ከነሙሉ ንብረቶች የሐራጅ መነሻ 27,548,162.07 (ሃያ ሰባት ሚሊዮን አምስት መቶ አርባ ስምንት ሺህ አንድ መቶ ስልሳ ሁለት ከ07/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 27 ቀን 2019 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ8:00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፤ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ C.P.O የሚያመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት/ ስም C.P.O አሠርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ግኘው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን ፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በሕጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Court-ordered auction of Dashiyang Manufacturing paint factory in Debre Berhan, Gendebel Bulen kebele, with all assets, on 11,342.36 sq m. Bidders must visit beforehand and deposit a verified CPO for 1/4 of the property estimate; winner pays full price within 15 days.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender