Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
  • Address Addis Ababa Ethiopiaq, Phone: +251112730852
  • Website
  • Deadline27 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየመነሻ ዋጋ 1/4 (CPO)
  • opening dateህዳር 18 ቀን 2019 ዓ/ም (ምዝገባ እንደተጠናቀቀ)
  • Categories Land , House, Building And Warehouse , Sales, Disposals And Foreclosure

የንግድ ቤት ሐራጅ ሽያጭ (ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13፣ ይዞታ 197 ካ/ሜ፣ ግንባታ 664 ካ/ሜ) - በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት እነ የሟች አቶ አንድዬ ተሰማ ሀይሉ ሚስት እና ወራሾች እና የፍ /ባለዕዳ አቶ ገብረእየሱስ ደስታ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/310432 በ18/06/2016ዓ.ም እና በኮ/መ/ቁ/319967 በ02/11/2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13 የካርታ ቁጥር የካ/205902/11 የሴሪያል ቁጥር 0123659 የሆነ ይዞታ በልማት ምክንያት በመፍረሱ የተሰጠው ምትክ ቦታ ሲሆን በአቶ ገብረእየሱስ ደስታ ስም የተመዘገበ የቤቱ አገልግሎት ለንግድ የሆነ የይዞታ ስፋት 197 ካ/ሜ አጠቃላይ የተገነባው ግንባታ የቤቱ ስፋት 664ካ/ሜ የሆነ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 23,413,940.68 (ሃያ ሶስት ሚሊዮን አራት መቶ አስራ ሶስት ሺህ ዘጠኝ መቶ አርባ ከ68/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 18 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት/ ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Court-ordered auction sale of a commercial building in Lemi Kura Sub-city, Woreda 13: 197 sqm land with 664 sqm built area. Bidders must deposit 25% of the starting price as CPO via Commercial Bank of Ethiopia; the winner must pay the full amount within 15 days.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender