የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ውበትና አረጓዴ ልማት ቢሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Addis Ababa city Urban Beautification and Green Development Bureau (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ)
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር የከ/ው/አ/ል/ቢሮ/ግ/ጨ 01/2018 ዓ.ም
በዚህ መሰረት:- የከ/ው/አረ/ል/ቢሮ 2018 በጀት ዓመት በሎት (1) የፅዳት ዕቃዎች፣ በሎት (2) የደንብ ልብስ፣ በሎት (3) የተሽከርካሪ መለዋወጫ/ጌጣጌጥ፣ በሎት (4) የችግኝ ጣቢያ ግብዓት፣ በሎት(5) የእስቴሽነሪ ዕቃዎች እና በሎት (6) ቋሚ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተለውን ማሟላት አለባቸው።
- በዘርፉ የተሰማሩ እና የዘመኑን የግብር የተከፈለበት፤ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት (Tin No) ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑበት ሰርተፊኬት፤ በአቅራቢነት የተመዘገቡና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ10 የስራ ቀናት ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ውበት እና አረንጓዴ ልማት ቢሮ የመንግስት ግዥ ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን፣ አድራሻችን የካ/ክ/ከተማ ቀበና አካባቢ ኬንያ ኢንባሲ ፊት ለፊት 2ኛ ፎቅ ግዥ ዳይሬክቶሬት ክፍል እንገኛለን።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳችሁን ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦሪጂናል እና አንድ ኮፒ፣ ፋይናሻል አንድ ኦሪጂናል እና አንድ ኮፒ ለየብቻ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ በጥንቃቄ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ ይህ ማስታወቂያ በወጣ እስከ 11ኛው የስራ ቀናት ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥኖች ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት (1) ብር 10,000፣ ለሎት (2) ብር 60,000፣ ለሎት (3) ብር 100,000፤ ለሎት (4) ብር 150,000 እና ለሎት (5) ብር 20,000 ለሎት (6) ብር 50,000 በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በወጣ በ11ኛው የስራ ቀናት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ግዥ ዳይሬክቶሬት ክፍል ይከፈታል።
- የጨረታ ማስከበሪያ አሸናፊዎች ተለይቶ ውል እስኪፈፅሙ እንደተያዘ ይቆያል።
- ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸውን ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ 10% የውል ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) በቢሮው ስም የተዘጋጀውን በማስያዝ በሰባት ቀን ውስጥ ውል ተዋውሎ ወደ ስራ መግባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚደርስ ሰነድ ሳይከፈት ለተጫራቹ ይመለሳል።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ላይ ለውጥ ማሻሻያ ማድረግ ወይም ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
- ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝራቸውን በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ሞልተውና በእያንዳንዱ ገፅ ላይ ማህተም እና ፊርማ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሰረት የሚወዳደሩበትን ዋጋ ቫትን (VAT) ያካተተ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች ጨረታ ለማስገባት በምትመጡበት ጊዜ ቴክኒካል ኮፒና ኦርጂናል፣ ፋይናንሻል ኮፒና ኦርጂናል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ለየብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0115 58 11 79 ደውለው ይጠይቁ።
- ቢሮው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ሰነዱን ለመግዛት በምትመጡበት ጊዜ በመስኩ የተሰማራችሁበትን ንግድ ፍቃድ ኮፒ መያዝ እንዳትረሱ።
- ዝርዝር ዕቃዎቹን ለማየት በ telegram ገፃችን https://t.me/addisabebagreenarea እና
- Facebook ገፃችን https://www.facebook.com/aaurbanbeutification
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ውበትና አረጓዴ ልማት ቢሮ
አዲስ አበባ
