በየካ ክ/ከተማ በወረዳ 08 የብሩህ ተስፋ ቅ/አ/አ/ደ/እና መ/ደ/ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ሎት 1. የደንብ ልብስ እና የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት፣ ሎት 2. የጽሕፈት መሳሪያ እቃዎች፣ ሎት 3 አላቂ የህክምና ዕቃዎች፣ ሎት 4. አላቂ የትምህርት ዕቃዎች፣ ሎት 5. የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 6 የተለያዩ መሳሪያዎች፣ ሎት 7. ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣ ሎት 8. ፕላንት ማሽነሪ፣ ሎት 9. የፕላንት ማሽነሪ ጥገና በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የካ ክ/ከተማ በወረዳ 08 የብሩህ ተስፋ ቅ/አ/አ/ደ/እና መ/ደ/ት/ቤት
አንደኛ ዙር ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር፡- 001/2018
በየካ ክ/ከተማ በወረዳ 08 የብሩህ ተስፋ ቅ/አ/አ/ደ/እና መ/ደ/ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ሎት 1. የደንብ ልብስ እና የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት፣ ሎት 2. የጽሕፈት መሳሪያ እቃዎች፣ ሎት 3 አላቂ የህክምና ዕቃዎች፣ ሎት 4. አላቂ የትምህርት ዕቃዎች፣ ሎት 5. የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 6 የተለያዩ መሳሪያዎች፣ ሎት 7. ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣ ሎት 8. ፕላንት ማሽነሪ፣ ሎት 9. የፕላንት ማሽነሪ ጥገና በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው። ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፣ በመሆኑም ት/ቤቱ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
|
ሎት ቁጥር |
በጀት ኮድ |
የእቃ/ አገልግሎት ዝርዝር |
የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ መጠን |
|
ሎት 1 |
6211 |
የደንብ ልብስ እና የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት |
7,500 |
|
ሎት 2 |
6212 |
የጽሕፈት መሳሪያ እቃዎች |
4,000 |
|
ሎት 3 |
6214 |
አላቂ የህክምና ዕቃዎች |
918 |
|
ሎት 4 |
6215 |
አላቂ የትምህርት ዕቃዎች |
5,000 |
|
ሎት 5 |
6218 |
የፅዳት ዕቃዎች |
4,000 |
|
ሎት 6 |
6219 |
የተለያዩ መሳሪያዎች |
2,000 |
|
ሎት 7 |
6313 |
ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች |
10,000 |
|
ሎት 8 |
6314 |
ፕላንት ማሽነሪ |
8,000 |
|
ሎት 9 |
6244 |
ለፕላንት ማሽነሪ ጥገና |
6,000 |
- የሀገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ሊኖራቸው ይገባል፡፡
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡና በግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን ጨረታ ላይ መሳተፍ እንዲችሉ የተሰጠ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን አለባቸው።
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ ሲፒኦ በእያንዳንዱ ሎት በተቀመጠው መሰረት ማቅረብ አለባቸው። ጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት ከሆኑ ከአደራጃቸው አካል መደራጀታቸውን በጨረታ ዋስትና ስራ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 9 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የእቃውን ናሙና ዝርዝር ለግዥ ክፍል ገቢ ማድረግ አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ ሲያቀርቡ ቫት ያጠቃለሉና ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች አሟልተው አንድ ወጥ የሆነ ዋናና ቅጂ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ /ፖስታ/ በብሩህ ተስፋ ቅ/አ/አ/ደ/እና መ ደ/ት/ቤት ፋይናንስ ክፍል የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ በ11ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብሩህ ተስፋ ቅ/አ/አ/ደ/እና መ/ደ/ት/ቤት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 9 ይከፈታል።
- አስራ አንደኛው ቀን በስራ ቀን ካልዋለ በቀጣዩ በስራ ቀን ልክ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዕቃ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
- የት/ቤቱ ጠቅላላ ለጨረታ ከቀረበው እቃ እስከ 25% መቀነስም ሆነ መጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾቹ የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ጠቅላላ ዋጋ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ውል ከተዋዋሉበት ጊዜ አንስቶ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ለ60 ቀናት ይሆናል፡፡
- ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- አሸናፊ ድርጅት የግዥ ትዕዛዝ ከደረሰበት ቀን ጀምሮ በ5/አምስት/ የስራ ቀናት ውስጥ ማቅረብ የሚችሉ እና የሚወዳደሩባቸው እቃዎች ናሙና ላይ ያሉ መሆን አለባቸው፡፡ የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ በራሱ ትራንስፖርት በብሩህ ተስፋ ቅ/አ/አ/ደ/እና መ/ደ/ት/ቤት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርት ሳያሟሉ በጨረታው ላይ ለመሳተፍ መሞከር ከጨረታው ያሰርዛል፡፡
- ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ- 22 ማዞሪያ ከትራፊክ ጽ/ቤት ወደ ሾላ ገበያ በሚወስደው ቀጭን አስፓልት ታቦት ማደሪያ ፊት ለፊት ወይም በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ጽ/ቤት አጠገብ ነው፤ ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011-6-66-38-77 መደወል ይችላሉ፡፡
የካ ክ/ከተማ በወረዳ 08 የብሩህ ተስፋ ቅ/አ/አ/ደ/እና መ/ደ/ት/ቤት
