Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethio Engineering Group (ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ)
  • Address ሜክሲኮ በሚገኘው የግሩፑ ዋና መስሪያ ቤት ብሎክ <A> ቢሮ ቁጥC MBD 002 ግብይትና ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት መምሪያ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 251986333388
  • Websitehttps://ethioengineering.com/
  • Deadline23 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Security50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/
  • opening date2025-10-23 00:00:00
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ከሜክሲኮ ወደ ሳር ቤት በሚወስደው ዋና መንገድ ላይ ከሚገኙት ህንፃዎች በሎክ-Aን ለተለያዩ አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።

Ethio Engineering Group (ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር፡- ኢኢግ/ግቢዴ/ብግጨ/001/2018

 

ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ከሜክሲኮ ወደ ሳር ቤት በሚወስደው ዋና መንገድ ላይ ከሚገኙት ህንፃዎች በሎክ-Aን ለተለያዩ አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቶች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የተሰማሩበት የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣
  2. የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ወይም የቲኦቲ ተመዝጋቢ ፍቃድ፣
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣
  4. የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
  5. ተጫራቹ የሀገር ውስጥ፣ የዓለም አቀፍ ለትርፍ ያልተቋቋመ የእርዳታ ድርጅት (NGO) ወይም የሲቪል ማህበራት ከሆነ ህጋዊ ሰውነት ያለው ማረጋገጫ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል።

 

ተ.ቁ

የሎት ቁጥር

የሎት መጠሪያ ስም

የሰነድ መሸጫ ዋጋ ብር

የጨረታ ማስከበሪያ ብር

1

1

ለባንክና ኢንሹራንስ፣ ለሱፐር ማርኬት፣ለዘመናዊ ቢሮ ለካፌና ሬስቶራንት ለትምህርት ቤት፤ ለተለያዩ ምርት ማሳያዎች እንዲሁም ለመሳሰሉት አገልግሎቶች

 

500.00

 

50,000.00

 

  1. ተጫራቹ ኢንቨስተር ከሆነ የኢንቨስትመንት ፈቃድ፤ የንግድ ማኅበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሑፍ፣ የሙያ አገልግሎት ሰጪ ከሆነ የሙያ ፈቃዱን ፎቶ ኮፒ ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል። ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ አዲስ አበባ ሜክሲኮ በሚገኘው የግሩፑ ዋና መስሪያ ቤት ብሎክ <A> ቢሮ ቁጥC MBD 002 ግብይትና ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት መምሪያ በመቅረብ ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ከዚህ በታች በተመለከተው መሰረት የማይመለስ ብር 500 በመክፍል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  2. ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበውን ሰነድ የኪራይ ዋጋ በግለፅ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ቴክኒካል ኦርጂናልና ኮፒ እና ፋይናሽያል ኦርጂናልና ኮፒ ለየብቻቸው ማስገባት አለበት፡፡
  3. ተጫራቾች የተጠቀሱትን ሰነዶች በመግዛት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ህንፃውን መመልከት ይችላሉ።
  4. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ግዜ ሳይገኝ ቢቀር ጨረታው ከመከፈት አይስተጓጎልም።
  5. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራች አሸናፊነቱ በተገለፀ ከ7 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቀርበው መዋዋል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ውሉን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ ተዋውሎ ካልጨረሰ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለግሩፑ ገቢ ይደረጋል፡፡
  6. ግሩፑ ባወጣው ጨረታ ሰነድ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይሆናል።
  7. ግሩፑ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- +251986333388 ወይም +251986333344 ደውሎ መጠየቅ፡፡

 

ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ

 

Save Tender