Tender Detail

Tender Details

  • Company አማራ ደን ኢንተርፕራይዝ
  • Address ባህር ዳር ከተማ በሚገኘው የድርጅቱ ቅጥር ግቢ, Phone: 0583202985
  • Website
  • Deadline22 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security2%
  • opening date2025-10-22 00:00:00
  • Categories Forest And Tree Sales

በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት በማዕ/ጎንደር ዞን ጭልጋ ወረዳ ባሉ ቀበሌዎች የመንግሥት ደን ውስጥ ያለውን የፈ/ጽድ 5,182.68 ሜ/ኩብ እና ነጭ ባህርዛፍ 671.41 ሜ/ኩብ በድምሩ 5,853.44 ሜ/ኩብ ቁም ደን፣ በምስ/ጎጃም ዞን ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ምጣድ ዱር የመንግሥት ደን ውስጥ ያለውን 620.11 ሜ/ኩብ የፈ/ጽድ ቁም ደን እና በአዊ ዞን ባንጃና ፋግታ ለኮማ ወረዳዎች ሳንኪት ልደታና አረጽ ቀበሌ መርጊ፣ችርሃና በተርያ የመንግሥት ደን ውስጥ የሚገኘውን 7,593.73 ሜ/ኩብ የፈ/ጽድ ቁም ደን እንዲሁም በደ/ታቦር እንጨት መሰንጠቂያ ማሽን የተመረተ 87.14 ሜ/ኩብ የፈ/ጽድ ጣውላ ምርት ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

አማራ ደን ኢንተርፕራይዝ


የቁም ደንና ጣውላ ምርት ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት በማዕ/ጎንደር ዞን ጭልጋ ወረዳ ባሉ ቀበሌዎች የመንግሥት ደን ውስጥ ያለውን የፈ/ጽድ 5,182.68 ሜ/ኩብ እና ነጭ ባህርዛፍ 671.41 ሜ/ኩብ በድምሩ 5,853.44 ሜ/ኩብ ቁም ደን፣ በምስ/ጎጃም ዞን ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ምጣድ ዱር የመንግሥት ደን ውስጥ ያለውን 620.11 ሜ/ኩብ የፈ/ጽድ ቁም ደን እና በአዊ ዞን ባንጃና ፋግታ ለኮማ ወረዳዎች ሳንኪት ልደታና አረጽ ቀበሌ መርጊ፣ችርሃና በተርያ የመንግሥት ደን ውስጥ የሚገኘውን 7,593.73 ሜ/ኩብ የፈ/ጽድ ቁም ደን እንዲሁም በደ/ታቦር እንጨት መሰንጠቂያ ማሽን የተመረተ 87.14 ሜ/ኩብ የፈ/ጽድ ጣውላ ምርት ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

 

ስለሆነም ተጫራቾች:-

 

1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤መሆን ይኖርባቸዋል።

 

2. የሽያጩ መጠን 200,000.00/ሁለት መቶ ሺህ /ብር በላይ ከሆነ የተእታ /VAT/ ምዝገባ የምስክርወረቀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

 

3. ለጨረታ የቀረቡትን ቁም ደን /ምርቶች/ ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት በቦታው ተገኝተው ማየት ይችላሉ ።

 

4. የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ /ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ/ በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት ባሕርዳር ቀበሌ 14 አዲሱ መናኸሪያ ጀርባ እንስሳት ማዳቀያ ግቢ ውስጥ ከኢንተርፕራይዙ ቢሮ ቁጥር 06 እና በሁሉም ቅ/ጽ/ቤቶች የማይመለስ 200.00(ሁለት መቶ ብር ) በመከፈል መግዛት ይችላሉ።

 

5. ተጫራቾች ለመግዛት የሚፈልጉትን ምርት ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ/CPO/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

 

6. ተጫራቶች መግዛት የሚፈልጉትን ቁም ደን በኦሪጅናል ዋጋ መሙያ ቅጽ የሚገዙበትን ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ስምና አድራሻቸውን በመፃፍ ፈርመው በመሙያው ሰነዱ ላይ ማህተም በማስቀመጥ የታሸገውን የጨረታ ፖስታ በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06፣ደ/ብርሃንና ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ‹‹የቁም ደንና ጣውላ የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ›› ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 የሥራ ቀናት (ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ) እስከ መጨረሻው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ሳጥኑ ታሽጎ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ይሁን እንጂ ተጫራቾች ባይገኙም ይከፈታል።

 

7. ተጫራቾች የሚሞሉት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ 15% ተእታን አይጨምርም። ሆኖም አሸናፊው በአሸነፈበት ዋጋ ላይ 15% ተእታን ጨምሮ ይከፍላል።

 

8. ተጫራቾች ቁም ደኑን በተመለከተ ቅልቅል ደን ተብሎ የቀረበውን ክፍልፋይ ሁሉንም አይነት ምርት ከፍልፋይ እና የጣውላ ምርትን ሁሉንም ሎት/ምድብ በመሙላት ማንሳት ይጠበቅባቸዋል።

 

9. በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡

 

10. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለተጨማሪ መረጃ በስልከ ቁጥር ባ/ዳር 0582263095፣ ደ/ታቦር 0584410306 ደ/ብርሃን 0116375017: አንጅባራ 0582270485: ደ/ማርቆስ 0588719004/ ኮ/ቻ 0914716636 ደውሎ መጠየቅ ይችላል።

 

የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት

Save Tender