በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሀዌላ/ወ/ፋ/ል/ጽ/ቤት ለወረዳው ሴከተርመሥሪያ ቤቶች አላቂ የጽ/መሣሪያ እና የጽዳት ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የሲዳማ ብሔራዊ ክልልዊ መንግስት መንግስት የሀዌላ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ፅ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሀዌላ/ወ/ፋ/ል/ጽ/ቤት ለወረዳው ሴከተርመሥሪያ ቤቶች አላቂ የጽ/መሣሪያ እና የጽዳት ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት መጫረት የሚችሉት -
በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ የቲን ተመዝጋቢ የሆኑ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የጨረታ ማስከበሪያ ከሚያቀርቡት ዋጋ በባንክ የተረጋገጠ CPO 2% ማስያዝ የሚችሉ፣ የውል ማስከበሪያ ማስያዝ የሚችሉ፣ መልካም የሥራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችሉ የአቅራቢነት ምስክርወረቀት ያላቸው፣ እንዲሁም የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ከሀዌላ ወረዳ ፋይ/ል/ጽ/ቤት ከግዥ/ፋይ/ንብ/አስተዳደር ሥራ ሂደት ቀርበው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት እስከ ቦታው ድረስ በራሱ ወጪ ዕቃውን ማቅረብ አለበት፡፡
ስለዚህ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ ለ20/ሃያ/ተከታታይ ሥራ ቀናት የጽ/መሣሪያ እና የጽዳት ዕቃ የሚያቀርቡበትን ዋጋ በመግለጽ በፖስታ አሽገው ዘወትር በሥራ ሰዓት ሀዌላ/ወ/ፋ/ል/ጽ/ቤት ግ/ፋይ/ን/አስተዳደርሥራ ሂደት ከፍል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማኖር ይችላሉ።
ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባልተገኙበት በ20ኛው ቀን ሲሆን የፖስታ ሳጥኑ በ5፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ በ5፡ 30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
ዕለቱ የበዓል ቀን ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በተመሳሳይ ሰዓት በማግስቱ ይከፈታል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የሀዌላ ወረዳ ፋ/ል/ጽ/ቤት
