በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የም/ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ግዥ በነቀምት ከተማ ውስጥ በሚገኙ ግምጃ ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ነገሮችን በ1ኛው ዙር ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የምስራቅ ዕዝ ጠ/መምሪያ ግዥ ቡድን
የብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መ/ቁጥር. ምዕ/ግ/ጨ/A-01/2018
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የም/ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ግዥ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነቀምት ከተማ ውስጥ በሚገኙ ግምጃ ቤቶች ውስጥ የሚራገፉ የተለያዩ አይነት ፡-
-
-
- የስራ ልብስ ቱታ እና ኤርጌንዶ ጫማ
- አላቂ የቢሮ የፅሕፈት መሣሪያዎች
- የትምህርትና ሥልጠና መርጃ ዕቃዎች
- የሕሙማን ቀለቦች
- አላቂ የፅዳት ዕቃዎች
- የሚዲያ ዕቃዎች
- የኦፊስ ማሽን ጥገና መለዋወጫ ዕቃዎች
- የማሽነሪና የጀነሬተር ጥገና መለዋወጫ ዕቃዎች
- ለቤቶች እድሳት የሚውሉ ሕንፃ መሣሪያዎች ሲሆኑ፤
-
ከላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በ1ኛው ዙር ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
በመሆኑም በዚህ ጨረታ ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ፡-
- አግባብ ያለው በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤
- የቫት ሰርተፍኬት
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ፤
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ መሆኑን ማስረጃ፤
- በንግድ ስያሜው መሠረት የተዘጋጀና የተረጋገጠ ወቅታዊ የባንክ ስቴትመንት ማቅረብ የሚችል፤
- የጨረታ ማስከበሪያ /2%/ ፡- ከባንክ የተረጋገጠ CPO ማቅረብ አለባቸው፤
የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ነቀምት በሚገኘው የምዕ/ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ የቀድሞ የኢትዮጵያ ገበሬዎች ማኅበር /ኢገማ/ ግቢ ውስጥ በሚገኘው ግዥ ቢሮ በመምጣት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከ ከመስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
የጨረታ ማስረከቢያ /CPO/ መጠን
-
-
- የሥራ ልብስ ቱታ እና ኤርጌንዶ ጫማ.......19,870.62
- አላቂ የቢሮ የፅሕፈት መሣሪያዎች.............3,869.58
- የትምህርትና ሥልጠና መርጃ ዕቃዎች…………3,864.68
- የሕሙማን ቀለቦች……………………………. 25,362.55
- አላቂ የፅዳት ዕቃዎች……………………………………30,306.93
- የሚዲያ ዕቃዎች…………………………3,282.01
- የኦፊስ ማሽን ጥገና መለዋወጫ ዕቃዎች………. 4,999.05
- የማሽነሪና የጀነሬተር ጥገና መለዋወጫ ዕቃዎች .......4,112.40
- ለቤቶች ዕድሳት የሚውሉ ሕንፃ መሣሪያዎች…………. 60,564.84
-
- ጨረታው ማክሰኞ ጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ/ም ከረፋዱ 3.00 ሠዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ጨረታው ማክሰኞ ጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ/ም ከረፋዱ 3.30 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በነቀምት ከተማ ምዕ/ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ የቀድሞ ኢገማ ግቢ ውስጥ በሚገኘው አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ያንዱን ዕቃ ዋጋ ከመሙላታቸው በፊት በጨረታ ሰነዱ ላይ የቀረበውን ስፔስፊኬሽን በአግባቡ ማንበብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለጨረታ ሲመጡ አስፈላጊ የሚባሉ እና ግዥ ፈፃሚው የሚያሳውቀው የዕቃዎችን ሳምፕል /ናሙና/ ማቅረብ አለባቸው።
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች የእያንዳንዱ ዕቃ ዋጋ ከሞሉ በኋላ የሚያቀርቡት ዕቃዎች ብራንድ 1 ስሪት ወይም የዕቃውን ጥራት ደረጃ ተዘጋጅቶ በቀረበው ፎርም በግልፅ ተሞልቶ ማኅተም ተደርጎበት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻው መቅረብ አለበት።
መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ ህጋዊ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ፡- ስልክ. 057 660 3275 መደወል ይቻላል።
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የም/ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ (ነቀምት)
