በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቅ/ጽ/ቤቱ እና በስሩ የሚገኙ መጣቢዎች ተይዘው እና ተወርሰው የሚገኙ የሞተር ሳይክል እና የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ የአልባሳት ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የመገናኛ መሳሪያዎች፣ ኮስሞቲክስ እና የንፅጽና መጠበቂያ ዕቃዎች፣ የቤት ውስጥ መገልገያ እና ማስዋቢያ ዕቃዎች፣ ምግብ ነክ ዕቃዎች፣ ሲሚንቶ እና ጂፒሰም፣ እንዲሁም ሎሎች ዕቃዎች በግልጽ እና በሐራጅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 11/2018
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቅ/ጽ/ቤቱ እና በስሩ የሚገኙ መጣቢዎች ተይዘው እና ተወርሰው የሚገኙ የሞተር ሳይክል እና የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ የአልባሳት ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የመገናኛ መሳሪያዎች፣ ኮስሞቲክስ እና የንፅጽና መጠበቂያ ዕቃዎች፣ የቤት ውስጥ መገልገያ እና ማስዋቢያ ዕቃዎች፣ ምግብ ነክ ዕቃዎች፣ ሲሚንቶ እና ጂፒሰም፣ እንዲሁም ሎሎች ዕቃዎች በግልጽ እና በሐራጅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ ቅድመ ሁኔታዎች እና መስፈርቶች ማሟላት የምትችሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃዎች ጋር ተዛማችነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ሰለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸውን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና መለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የግልጽ ጨረታ ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00-12፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00-6፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በጽ/ቤታችን የእለት ገቢ ገንዘብ ሰብሳቢ ቢሮ ቁ.ር 16 በመገኘት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ መዝጊያው ቀን ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡
- በግልፅ ጨረታው ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ዋስትና (CPO) እንዲሁም በሐራጅ ጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎችንም በተመለከተ ማስያዝ ያለባችሁ የሲ.ፒ.ኦ መጠን በየኮዱ የሚለያይ ስለሆነ ከጨረታ ደንብ ላይ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ በጉምሩክ ኮሚሽን በሞያሌ ቅርንጫፍ ስም በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚካሄደው በሞያሌ ቅ/ጽ/ቤት ሲሆን ተጫራቾች (ሕጋዊ ወክሎቻቸው) ባሉበት ወይም ታዛቢ ፊት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣው ከታተመበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር እሰከ 7ኛው ቀን ድረስ ለጨረታ የቀረቡ ዕቃዎች ናሙና በሞያሌ እና በሁሉም መጣቢያ የሚገኙ መጋዝኖቻችን እየሄዱ መመልከት አለባቸው።
- ጨረታው የሚካሄደው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር በ8ኛው ቀን ሲሆን ጨረታው ከጠዋቱ 3፡45 ተዝግቶ 4፡00 (አራት ሰዓት) ላይ ይከፈታል፡፡
- ከላይ በተራ.ቁጥር 6 በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 8ኛው ቀን የሥራ ቀን ሳይሆን ሲቀር ጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡
- ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፉ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታውን ውጤት ከተገለጸ በ3 ቀናት ውሰጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ከላይ በተራ ቁጥር 9 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት COP ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0464441415/0464441564 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
