Tender Detail

Tender Details


በኢሉአባቦራ ዞን የዳሪሙ ሆስፒታል ዕቃዎችን በ2018 ዓ.ም. የበጀት ዘመን ለሆስፒታል አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በኦሮሚያ ጤና ቢሮ የዳሪሙ ሆስፒታል


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በኢሉአባቦራ ዞን የዳሪሙ ሆስፒታል ዕቃዎችን በ2018 ዓ.ም. የበጀት ዘመን ለሆስፒታል አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  • የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች
  • የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የቢሮ ዕቃዎች ወይም ፈርኒቸሮችን
  • የደንብ ልብሶች፣ የተለያዩ ጎማዎች፣ የተለያዩ ህትመቶች

በዚሁ መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
  2. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ግብር የከፈሉበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተመሰከረ ቼክ ወይም ሲፒኦ ከውድድር ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. አሸናፊ ተጫራቾች ለመልካም ሥራ አፈፃፀም የጠቅላላ ዋጋውን 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች ጋዜጣው ከወጣበት ቀን አንስተው ለተከታታይ የሥራ ቀን 15 ቀናት የጨረታውን ሰነድ ከኢሉባቦር ዞን ዳሪሙ ሆስፒታል በመውሰድ ሁሉንም ሰነድ አንድ መቶ ብር በመግዛት ዋጋውን ሞልተው ከገዙበት ቀን ጀምሮ አስከ 17/2/2018 ቀን ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ጽ/ቤት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በ 17/2/2018 ዓ.ም እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. የጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ17/2/2018 በ 8፡30 ሰዓት በግልፅ ይከፈታል፡፡
  9. የዕቃው ማስረከቢያ ቦታ ዳሪሙ ሆስፒታል ሆኖ ጠቅላላ ወጪ የሻጩ ግዴታ ናቸው፡፡
  10. በሌላ ተጫራቾች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  11. የዕቃውን ብዛት ከውድድር በኋላ የሚገለፅ ይሆናል፡፡
  12. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡ ከተራ ቁጥር 1- 7 በተጠቀሰው ያልተስማማ በጨረታው መሳተፍ የለበትም፡፡
  13. ለተጨማሪ መረጃ በስልከ ቁጥር 0474440319/0948112134 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡

 

በኦሮሚያ ጤና ቢሮ የዳሪሙ ሆስፒታል

 

Save Tender