Tender Detail

Tender Details


የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በ2018 የበጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነገሮች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

Adama Hospital Medical College (የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በ2018 የበጀት ዓመት

  1. Air Conditioner (AC) ለአንደኛ ጊዜ ለማስጠገን
  2. የተለያዩ የመኪና ጎማ ለአንደኛ ጊዜ ለመግዛት
  3. Medical Equipment spare part and Accessories ለሁለተኛ ጊዜ ለመግዛት
  4. የተለያዩ የመማርና ማስተማር እና ለ “CPD center” ዶክመንቶች ኮፒ ማድረግ (መግዛት) እና መጠረዝ ለአንደኛ ጊዜ ለማሰራት በግልፅ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶች የምታሟሉ ነጋዴዎች መወዳደር ትችላላችሁ።

  • 2017 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ በዘርፉ ያላችሁ እንዲሁም የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈለ።
  • ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆኑ መረጃ ማቅረብ የሚችል
  • በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ፅ/ቤት በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባችሁን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ።
  • ተጫራቾች የማያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ ኮፒና ኦርጅናል ብቻ በተለያየ ፖስታ ማሸግ አለባቸው።
  • ስርዝ ድልዝ ያለው የማይታይ የጨረታ ሰነድ ወይም የዋጋ ዝርዝር ተቀባይነት የለውም።
  • ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ የውል ማስከበሪያ የአሸነፉበትን 10% ማስያዝ የሚችል።
  • ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከኮሌጁ ግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት ክፍል ዘወትር በስራ ሰአት የማይመለስ ለእያንዳንዱ ጨረታ 200 ሁለት መቶ በመክፈል የጨረታ ሰነዱ መውሰድ አለባቸው።
  • በተለያዩ የመማር ማስተማር እና "CPD center" ዶክመንቶችን ኮፒ ማድረግ (ማባዛት) መጠረዝ ከአዳማ ከተማ ጥቃቅንና አነስተና ኢንተርፕራይዝ መደራጀቱን የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል።
  • የMedical Equipment spare part and Acessories ጨረታው የሚከፈተው በ11/02/2018 ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  • Air Conditioner (AC)* ጨረታው የሚከፈተው በ11/02/2018 ከቀኑ 9:30 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  • የተለያዩ የመኪና ጎማ ጨረታው የሚከፈተው በ12/02/2018 ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሱቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  • የተለያዩ የመማርና ማስተማር እና "CPD center" ዶክመንቶች ኮፒ ማድረግ (ማባዛት) እና መጠረዝ በ12/02/2018 ከቀኑ 9:30 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  • ተጫራቾች የሚሞሉትን ዋጋ በመስሪያ ቤቱ ሰነድ ብቻ ላይ መሆን አለበት።
  • ጨረታ ማስከበሪያ
  • ለ Air Conditioner (AC) የተለያዩ የመኪና ጎማ "Medical Equipment spare part and Accessories" በእያንዳነዱ ጨረታ ለየብቻ 20,000 (ሃያ ሺ) ብር እና
  • ለተለያዩ የመማርና ማስተማር እና በ*CPD center" ዶክመንቶች ኮፒ ማድረግ (ማግዛት እና መጠረዝ 10,000 በ CBE, CBO. እና በ Singe" ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማስያዝ ሚችል መሆን አለበት።
  • መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0228123956 ደውለው መረዳት ይችላሉ።

 

የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ

 

Save Tender