Tender Detail

Tender Details

  • Company በወሎ ዩኒቨርሲቲ የላኮመንዛ ንግድና ማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ
  • Address ወሎ ዩኒቨርሲቲ ደሴ ካምፓስ ብሎክ 20 ቢሮ ቁጥር 2023 ፡ አማራ ክልል፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0914711156
  • Website
  • Deadline18 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceለእያንዳንዱ መድኃኒት ቤት ብር 200.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityለእያንዳንዱ መድኃኒት ቤት ብር 25,000.00 (CPO)
  • opening dateበዚሁ ቀን ከጧቱ 4:30፤ ቀኑ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን
  • Categories Pharmaceutical Products , Medical Equipment And Supplies

የወሎ ዩኒቨርሲቲ ላኮመንዛ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ ለደሴና ኮምቦልቻ መድኃኒት ቤቶች የሰው መድኃኒቶች ግዥ

በወሎ ዩኒቨርሲቲ የላኮመንዛ ንግድና ማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ


የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 002/2019

በወሎ ዩኒቨርሲቲ የላኮመንዛ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ ስር በደሴ እና ኮምቦልቻ ለሚገኙት መድኃኒት ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የሰው መድኃኒቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::

ስለሆነም :-

  1. ተጫራቾች፤- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ በዘርፉ አግባብ ያለውና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር/ቲን/፤ የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ተያያዥ ማስረጃዎችን ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል::
  2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በኢትዮጵያ በታወቀ ባንክ የተመሰከረለት ለእያንዳንዳቸው መድኃኒት ቤት የብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ) CPO በድርጅቱ ትክክለኛ ስም ላኮመንዛ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ በማሰራት ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ መግዣ ለእያንዳንዳቸው መድኃኒት ቤት የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከኢንተርፕራይዙ አስ/ፋይ/አገ ዘርፍ ግዥ ቡድን ቢሮ መግዛት ይችላሉ::
  4. ጨረታውን የሚያቀርበውና የሚፈርመው ወኪል ከሆነ ከሚመለከተው ውክልና ሰጭ (መዝጋቢ አካል) የተሰጠ ህጋዊ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል::
  5. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዕቃ ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ በጨረታ ሰነዱ በመሙላት ዋናና አንድ ኮፒ በታሸገ ፖስታ የተጫራቹ ድርጅት ማኅተም ተደርጎበትና ተፈርሞ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ደሴ ካምፓስ ብሎክ 20 ቢሮ ቁጥር 2023 በሚገኘው የኢንተርፕራይዙ አስ/ፋይ/አገ /ዘርፍ ግዥ ቡድን ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት አለባቸው::
  6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተራ ቁጥር 5 በተጠቀሰው ቀን እና ቢሮ ከጧቱ 4:30 በግልፅ ይከፈታል፤ ቀኑ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል::
  7. ተጫራቾች ባይገኙም ሰነዳቸው የተሟላ ሆኖ ከተገኘ በሌሉበት የሚከፈት ይሆናል::
  8. ከተጠቀሰው ሰዓት ዘግይቶ የሚመጣ የመወዳደሪያ ሀሳብ ወይም ጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም:: ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ ያሸነፉትን ዕቃ በደሴ እና ኮምቦልቻ የኢንተርፕራይዙ ንብረት ክፍል የሚገኝበት ቦታ በማቅረብ ማስረከብ ይኖርባቸዋል::
  9. ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ ላሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10% በኢትዮጵያ በታወቀ ባንክ የተመሰከረለት CPO ውል ማስከበሪያ በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
  10. አሸናፊ ተጫራች በውሉ ውስጥ የተካተቱትን ህጎች ማክበር አለባቸው::
  11. ኢንተርፕራይዙ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ማሳሰቢያ:የጨረታ ሰነድ ሲያስገቡ ለየትኛው መድኃኒት ቤት ማለትም ለደሴ ወይም ለኮምቦልቻ መሆኑን በሰነዱ ማሸጊያ ላይ መግለጽ ይጠበቅባችኋል::

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0921269119/0910449497 መጠቀም ይችላሉ

ላኮመንዛ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ

✨ messages.ai_summary
Wollo University Lakomenza Trade and Consultancy Enterprise seeks suppliers of various human medicines for its pharmacies in Dessie and Kombolcha. Bidders need a renewed licence in the field, trade registration, TIN, supplier registration and tax clearance. Open bid.
Save Tender