በቦሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 06 አስተዳደር ለ2018 ዓ.ም ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል።
በቦሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 06 አስተዳደር
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር፡- 001/18
በቦሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 06 አስተዳደር ለ2018 ዓ.ም ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 - አላቂ የቢሮ እቃ/ የፅሕፈት እቃዎች፣
- ሎት 2 - አላቂ የፅዳት እቃዎች፣
- ሎት 3 - የደንብ ልብስ፣
- ሎት 4 - ቋሚ እቃዎች፣
- ሎት 5 - የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣
- ሎት 6 - ህትመት ስራዎች (ውጤቶች)፣
- ሎት 7 - ትራንስፖርት አገልግሎት፣
- ሎት 8 - የጥገና አገልግሎት፣
- ሎት 9 - የመስተንግዶ አገልግሎት፣
ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል፡፡
- ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤
- የመንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ፤
- ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ከግብር አስገቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በየሎቱ 2% ማለትም፡-
|
ሎት |
የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና CPO በብር |
|
ሎት 1 |
20,000 |
|
ሎት 2 |
20,000 |
|
ሎት 3 |
20,000 |
|
ሎት 4 |
20,000 |
|
ሎት 5 |
20,000 |
|
ሎት 6 |
10,000 |
|
ሎት 7 |
15,000 |
|
ሎት 8 |
15,000 |
|
ሎት 9 |
10,000 |
- ማንኛውም ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በየሎቱ በመግዛት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር ፋ/ፅ/ቤት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 14 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በታሸገ ኤንቨሎፕ ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በ11ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጎ በዕለቱ በዛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተሰጠው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ ከሆኑ ላሸነፉበት እቃ ዋስትና ወይም የውል ማስከበሪያ CPO 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በተጨማሪ መስሪያ ቤቱ የጨረታውን 20% መቀነስ ወይም መጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ለመጫረት ሲመጡ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ናሙና የማይቀርብባቸው ቋሚ ዕቃዎች መስሪያ ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው።
- በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በመ/ቤቱ ግ/የስራ ሂደት ክፍል ድረስ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 011-8-67-81-29 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡- ከመገናኛ ወደ ጉርድ ሾላ በሚወስደው መንገድ ገባ ብሎ ውሃ እና ፋሳሽ ባለስልጣን ዋና መስሪያ ቤት ፊት ለፊት
በቦሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 06 አስተዳደር
