Tender Detail

Tender Details


በደ/ኢ/ክ/መንግስት በጌዴኦ ዞን የዲ/ዙ/ወ/ፋይ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለዲላ/ዙ/ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ቋሚና አላቂ የቢሮ ዕቃዎችን ማለትም ሎት1/ የጽህፈት መሣሪያ፣ሎት2/ ሞተር ሳይክል፣ሎት3/ ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት4 ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዲላ/ዙ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥና ፋ/አስ/ዋና/የስራ ሂደት ጪጩ


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በደ/ኢ/ክ/መንግስት በጌዴኦ ዞን የዲ/ዙ/ወ/ፋይ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለዲላ/ዙ/ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ቋሚና አላቂ የቢሮ ዕቃዎችን ማለትም ሎት1/ የጽህፈት መሣሪያ፣ ሎት2/ ሞተር ሳይክል፣ ሎት3/ ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት4 ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች

  • በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል
  • የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
  • የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
  • የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል

ከላይ በዝርዝር የተቀመጠውን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 15 ሥራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በሥራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 በመክፈል ከዲላ ዙ/ወ/ገቢዎች ጽ/ቤት በመቅረብ መግዛት ትችላላችሁ።

ማሳሰብያ

  • ተጫራቾች ሎት1/ ጽህፈት መሳሪያ 5000 /አምስት ሺህ ብር ብቻ
  • ተጫራቾች ሎት2/ ሞተር ሳይክል 5000 /አምስት ሺህ ብር ብቻ
  • ተጫራቾች ሎት3/ ኤሌክትሮኒክስ 5000 /አምስት ሺህ ብር ብቻ
  • ተጫራቾች ሎት4/ ፈርኒቸር 5000 /አምስት ሺህ ብር ብቻ
  • የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ፣ ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ቼክ ና በጥሬ ገንዘብ ማቅረብ ይቻላል፡፡
  • ተጫራቾች ዕቃዎች የሚሸጡበትን ዋጋ በተዘጋጀው ዝርዝር ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልተዉ አንድ ኦርጂናል ሰነድ እና ሁለት ኮፒ ሰነድ በተለያየ ፖስታ ካሸጉ በኋላ ከሲፒኦ ጋር በአንድ ትልቅ ፖስታ በሰም በማሸግ ማቅረብ ይገባቸዋል፡፡
  • ኦርጂናል ኮፒ ሰነድ ላይ ማንኛዉም አይነት ስርዝ ድልዝ /ፍሉድ/ የተስተካከለ በሚታይ መልኩ በድጋሚ ተጽፎ በተጫራቾች /በህጋዊ ተወካይ መፈረም አለበት፡፡
  • ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ ህጋዊ የድርጅት ማህተም ፊርማ ማረፍ አለበት፡፡
  • ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ወጥቶ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ ለ15 ለሥራ ቀናት ቆይቶ በ16ኛውቀን ጠዋት የጨረታ ሳጥን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ላይ ተጫራቾች/ህጋዊ ወከሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ስለሆነም የ16ተኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው በስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታው የሚከፈት ይሆናል፡፡
  • የጨረታ ሳጥን የሚገኘው በዲላ/ዙ/ወ/ፋይ/ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ግዥና ፋ/አስ/ዋና/ሥራ ሂደት ነው።
  • ተጫራቾች ጨረታውን ተወዳድረው ያሸነፉበትን ዕቃዎች በድላ/ዙ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤት ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ የማጓጓዝ፣ የማስጫን እና የማውረጃ ወጪ ችለው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ተጫራቾች በጨረታ ላይ መገኘት አለመገኘት የጨረታ ሂደቱን አያስተጓጉልም፡፡
  • መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ /በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ስልከ ቁ/ር 0970904657

ስልክ ቁ/ር 0912706413

 

በዲላ/ዙ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥና ፋ/አስ/ዋና/የስራ ሂደት

ጪጩ

Save Tender