በየካ ክ/ከተማ የወረዳ 08 ጨፌ ጤና ጣቢያ ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ የህክምና ሪኤጀንት አላቂና ቋሚ እቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በየካ/ክ/ከተማ ወረዳ 08 ጨፌ ጤና ጣቢያ
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ 1.1/18
በየካ ክ/ከተማ የወረዳ 08 ጨፌ ጤና ጣቢያ ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ የህክምና ሪኤጀንት አላቂና ቋሚ እቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት በጨረታው መሳተፍ ለምትፈልጉ ማንኛውም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሟላት ይኖርባችኋል፡፡
- ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ መስክ የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸውና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት ማሸነፉ እንደተገለፀለት የውል ማስከበሪያ የውሉን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ ህጋዊ እውቅና ካለው ባንክ ሲፒኦ በማቅረብ በ10 ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል መፈፀም የሚችል መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ (ፋይናንሻል ሰነድ) ኦርጅናል እና ኮፒ፣ ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ ብሎ በመለየት ለየብቻው በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ሕጋዊ ማህተምና ፊርማ በማድረግ በሎቱ በፖስታ በማሸግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ሰነዱን የአንዱን ዋጋ ቫትን ያካተተ በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ከላይ የተዘረዘሩትን የሚያሟሉ ተጫራቾች ለጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን 10 የስራ ቀናት የተዘጋጀውን ሰነድ ከየካ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ጨፌ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ላይ የረዳት ፋይናንስ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 413 ቀርበው በየሎቱ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ከፍለው ሰነዱን በመውሰድ
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያገለግል የሚጫረቱበት ዋጋ 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ የህክምና ሪኤጀንት አላቂና ቋሚ እቃ ሎት 1 በጨፌ ጤና ጣቢያ ስም ከታወቀ ባንክ በተረጋገጠ በሲፒኦ /CP.O/ ብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከገዙበት ጨረታ ሰነድ ውጭ ተሞልተው የሚመጡ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።
- ጨረታውም ማስታወቂያው ከወጣበት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ በ11ኛው ቀን ጠዋት 4:00 ሰዓት ላይ ጨረታው ታሽጎ በዚሁ እለት 4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በየካ ክ/ከተማ የወረዳ 08 ጨፌ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 409 በግልጽ ይከፈታል። ነገርግን ጨረታው የሚከፈትበት እለት ህዝባዊ/ሀይማኖታዊ በዓል ከሆነ ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ሌላ ማስታወቂያ ማውጣት ሳያስፈልግ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው አከፋፈት ስርአት ላይ በራሳቸው ፍቃድ ባይገኙ ጨረታው አይስተጓጎልም።
- ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ
ከመገናኛ ወደ ሲግናል በሚወስደው መንገድ ሱመያ መስጊድ ጀርባ ከማጂክ ት/ቤት አጠገብ
ስልክ ቁጥር:- 0118932878 ወይም 0916-51-87-02
በየካ/ክ/ከተማ ወረዳ 08 ጨፌ ጤና ጣቢያ
