በጉለሌ ክ/ከ/ወረዳ-1 ፋ/ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሉት የሚውል አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ አላቂ የፅዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት፣ በድጋሚ የወጣ የትራንስፖርት አገልግሎት፣ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች እንዲሁም የቋሚ ዕቃ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ጉ/ክ/ከ/ወ-1ፋ/02/2018
በጉለሌ ክ/ከ/ወረዳ-1 ፋ/ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሉት የሚውል አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ አላቂ የፅዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት፣ በድጋሚ የወጣ የትራንስፖርት አገልግሎት፣ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች እንዲሁም የቋሚ ዕቃ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም፣
- በዘርፉ ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ።
- የንግድ ፍቃድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- የግዥውን መጠን እንደ አስፈላጊነቱ 20% መጨመር ወይም መቀነስ የሚቻል መሆኑን።
- በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን ማስረጃ ከ(egpwww.ppa.gov.et) ማቅረብ የሚችሉ።
- ማንኛውም ተጫራች ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ሰነዱ በሚመለከተው ሰው ተሞልቶ ተፈርሞና ማህተም ተደርጎበት በጉ/ክ/ከ/ወ-1 ፋ/ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት።
- ጨረታው የሚያበቃው በ10ኛው የሥራ ቀን 11፡00 ሰአት ሲሆን በአስራ አንደኛው ቀን ጠዋት 3፡30 ተዘግቶ በእለቱ ከጠዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ሁሉም ተጫራቾች ሰነዱን ከገዙ በኋላ ናሙና ማቅረብ የሚቻል እቃዎች ላይ ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸዉ፣ ናሙና መቅረብ ሲገባ ያልቀረበ ከሆነ ግን ተቀባይነት የለውም፣ እንዲሁም ናሙና ለማቅረብ የሚያስቸግር ዕቃዎች በደንብ በሚታይ ፎቶ የተደገፈ እና በደንብ በሚታይ መልኩ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
- በድጋሚ የወጣ የትራንስፖርት አገልግሎትን በተመለከተ ቫት/ቲኦቲ ተመዝጋቢ የሆኑ ሁለቱም አቅራቢዎች መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
- አሸናፊው አቅራቢ ድርጅት በራሱ ትራንስፖርት ዕቃውን ተቋሙ ድረስ ማቅረብ አለበት።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይም ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም። ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታው በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ከጥቃቅን እና አነስተኛ በተመለከተ ካደራጃቸው መስሪያ ቤት የድጋፍ ደብዳቤ ምን አይነት ምርት እንደሚያመርቱ እና የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። የሃገር ውስጥ ምርት ችርቻሮ /ጅምላ ንግድ ከሆነ ደግሞ ከአምራቹ የተሰጣቸውን ፍቃድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ
- ሎት1. አላቂ የቢሮ ዕቃ 20,000.00 /ሃያ ሺ/ብር
- ሎት2. አላቂ የፅዳት ዕቃ 22,000.00 /ሃያ ሁለት ሺ/ብር
- ሎት3. የደንብ ልብስ 17,000.00 /አስራ ሰባት ሺ/ብር
- ሎት4. የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት 5,000.00 /አምስት ሺ/
- ሎት5. የትራንስፖርት አገልግሎት 10,000.00 /አስር ሺ/
- ሎት6. የመኪና መለዋወጫ 15,000 /አስራ አምስት ሺ/
- ሎት7. የቋሚ ዕቃ 5000 /አምስት ሺ/ብር ብቻ በባንክ በተመሠከረለት CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታውን ዝርዝር የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ ኮፒ በየሎቱ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር በመክፈል ከፋ/ጽ/ቤት አሮጌ ህንጻ 1ኛ ፎቅ መውሰድ ይችላሉ።
አድራሻችን፡- በጉለሌ ክ/ከ/ወ/1 ፋ/ጽ/ቤት በተለምዶ ሽሮሜዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ወደ ቁስቋም በሚወስደው መንገድ ላይ ሲሆን ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111230753/0111540864 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
ማሳሰቢያ ፡- እያንዳንዱ ተጫራች በሚያቀርበው ዋጋ ላይ የቫት ተመዝጋቢ ሆኖ ካልጨመረ እንደተጨመረ ተደርጎ ስለሚወሰድ VAT በመጨመር ሰነዱ ይቅረብ።
የትራንስፖርት አገልግሎትን በተመለከተ የቫት/ቲኦቲ ተመዝጋቢ ሆኖ ካልጨመረ እንደተጨመረ ተደርጎ ስለሚወሰድ VAT/ቲኦቲ በመጨመር ሰነዱ ይቅረብ።
በጉለሌ ክ/ከ/ የወረዳ 1 ፋ/ጽ/ቤት
