Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Agricultural Businesses Corporation (የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን)
  • Address ሳሪስ አቦ ፋፋ የምግብ አክሲዮን ጎን 200 ሜትር ገባ ብሎ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114709095
  • Websitehttps://ethioagri.com/
  • Deadline16 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Securityየጨረታ ማስከበሪያው የገንዘብ መጠን በየ ሎቱ የተለያየ ነው።
  • opening date2025-10-23 00:00:00
  • Categories 3- Wheel Vehicle, Motorcycles And Bicycles , Vehicle , Agricultural Materials , Machinery And Vehicles , Used Items , Vehicle Spare Parts

የኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ እና በቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሚገኙ ከዚህ በታች የተገለጹትን ያገለገሉ ንብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Ethiopian Agricultural Businesses Corporation (የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ እና በቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሚገኙ ከዚህ በታች የተገለጹትን ያገለገሉ ንብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

 

ሎት ቁጥር

የዕቃው አይነት

ሎት 1

የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች፣ ትራክተሮች፣ አጭዶ መውቂያዎች፣ ሞተርሳይክሎች እና ብስክሌቶች

ሎት 2

የተለያዩ ያገለገሉ የእርሻ መሳሪያዎች እና ተቀጽላ መሳሪያዎች

ሎት 3

የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች እና ሌሎች መሳሪያዎች

 

ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።

ሀ) ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እቃዎቹ በሚገኙበት በኮርፖሬሽኑ፣ በግባዓት እና በጎተራ እንዲሁም በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ማለትም (ሀዋሳ/ሻሎ፣ አሰላ/ጎንዴ፣ ቻግኒ፣ አርዳይታ፣ ሞጆ፣ ጊቤ፣ አዳማ፣ ሄረሮ እና ሮቤ) በመቅረብ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

ለ) የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የሚካሔደው ይህ ማስታውቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ክፍት ይሆናል፡፡ ጨረታውም በ10ኛው የስራ ቀን በ10፡00 ሰዓት ተዘግቶ የቅ/ጽ/ቤት ሰነዶች ተሰብስበው ከመጡ በኋላ በ15ኛው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን የመሰብሰቢያ አዳራሽ አዲስ አበባ ይከፈታል፡፡

ሐ) ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት ማለትም፡-

ሎት 1 - ለአነስተኛ ተሽከርካሪዎች ለእያንዳንዱ ለሚወዳደሩበት ተሸከርካሪ ብር 15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ ብር) እና

ለከባድ ተሽከርካሪዎች እና ተሳቢዎች፣ ለትራክተሮች እና ኮምባይነሮች ለእያንዳንዱ ለሚወዳደሩበት ተሽከርካሪ ዋጋ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር)፣

ሎት2 - ለእርሻ መሳሪያዎች እና ተቀጽላ መሳሪያዎች የመግዣ ዋጋውን ብር 10%፤

ሎት 3 - የተለያዩ መለዋወጫዎችና እና ሌሎች መሳሪያዎች የመግዣ ዋጋውን ብር 10% በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) በኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስም በማዘጋጀት ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

መ) ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ዕቃ የሚገዙበትን ዋጋ ከተጨማሪ ዕሴት ታክስ በፊት በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሠንጠረዥ ላይ በዝርዝር በማመላከት ማቅረብ አለባቸው፡፡

ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ከፋፋ የምግብ አክሲዮን ማህበር ጀርባ ወይም ከ EBG/ VOLVO ቀጥሎ ወደ ውስጥ በሚያስገባው መንገድ 100 ሜትር ገባ ብሎ

ስልክ ቁጥር:- 09-11-75-33-41/09-32-10-06-88/09-34-88-19-22

 

የኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን

 

Save Tender