Tender Detail

Tender Details


በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከዚህ በታች የተመለከቱትን

  1. ሎት1 የቢሮ ፈርኒቸር
  2. ሎት2 የኤሌክትሮኒክስ እቃ
  3. ሎት3 የተለያዩ የጽዳት ዕቃዎች
  4. ሎት4 አላቂ ዕቃዎች እና
  5. ሎት5 ሞተር ሳይክል ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቶች ከዚህ በታች በዝርዝር የተመለከቱ ሁኔታዎችን በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የአቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ እና የግብረ ከፋይ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ (bid security) ሎት 1 ሎት 5 እና ሎት 2 ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) እንዲሁም ሎት 3 እና ሎት4 10,000 (አስር ሺህ ብር) ማስያዝ አለባቸው።
  4. ማንኛውም ተጫራች ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ይህ ማስታውቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሰራ ሰዓት የማይመለሰ የታደሰ ንግድ ፍቃድና ተያያዥነት ያላቸው ሰነዶች ኮፒ ይዞ በመቅረብ ከግዥ ፋይናንሰ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 9 ቀርቦ ሰነዱን መግዛት ይችላል፡፡
  5. የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መመሪያ መሰረት ተሞልቶ አርጅናልና ኮፒ በማድረግ በሰም በታሸገ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ከተውና በሁሉም ዶክመንቶች የድርጅቱን ማህተም በመምታትና በመፈረም ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡ ጨረታው ሰነድ ማስገቢያ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ይሆናል፡፡
  6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀን በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት በማዕከላዊ ሲዳማ/ዞን ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ በይ/ዓለም ከተማ 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
  7. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ዕቃ እስከ ሲዳማ ብ/ክ/መንግስት በማዕከላዊ ሲዳማ/ዞን ፋይናንሰና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ በማውረድ ያስረክባል፡፡ አስቀድሞ ዕቃውን ናሙና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  8. ጨረታው የሚከፈትበት የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ይሆናል፡፡

ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ዝርዝር የጨረታ ሂደት በጨረታው ሰነድ መመሪያ ላይ ተገልጿል፡፡

ለበለጠ መረጃ 0916-406737 / 091616-4512 በመደወል መጠየቅ ይቻላል

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ

 

Save Tender