የስንቅ በጎ አድራነት ድርጅት በአፈዴሪ ሲቪክ ማህበረሰብ ባለስልጣን በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 በመዝገብ ቁጥር 5607 ግንቦት 4 ቀን 2013 ዓ/ም ፍቃድ ያገኘ ሀገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን ድርጅቱ የአንድ በጀት አመት ማለትም የ2017 በጀት አመት ያንቀሳቀሰውን ሂሳብ በተፈቀደላቸው አዲተሮች አዲት ማስደረግ ይፈልጋል።
ስንቅ በጎ አድራጎት ድርጅት
የኦዲት ሂሳብ ምርመራ የአገልግሎት
ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የስንቅ በጎ አድራነት ድርጅት በአፈዴሪ ሲቪክ ማህበረሰብ ባለስልጣን በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 በመዝገብ ቁጥር 5607 ግንቦት 4 ቀን 2013 ዓ/ም ፍቃድ ያገኘ ሀገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን ድርጅቱ የአንድ በጀት አመት ማለትም የ2017 በጀት አመት ያንቀሳቀሰውን ሂሳብ በተፈቀደላቸው ኦዲተሮች አዲት ማስደረግ ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን ያሟሉ ተጫራቾች መጫረት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን መስፈርቱም፡-
- ድርጅቱን ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል የኦዲተርነት የሙያ ደረጃ ፍቃድ ያላቸው።
- የንግድ ምዝገባ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ኦርጅናል ወይም የተገናዘበ ኮፒ የሚያቀርቡ፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና የሙያ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ፣
- ተጫራቾች ወቅታዊ ብቃታቸውን እና ሙያዊ ስነምግባራቸውን በተመለከተ ከፍቃድ ሰጭው አካል ከዋናው ኦዲት መ/ቤት ወይም ከኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝ እና አዲት ቦርድ ወይም ሂሳብ አዋቂዎችና የግል ኦዲተሮች ማህበር ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- የድርጅቱን የበጀት አመት ሂሳብ ኦዲት ለማድረግ በተሰጠው ጠቅላላ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ 2% ማስያዝ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ለሚያከናውነት ዝርዝር ተግባር በህግ ፊት ቀርበው እና የውል ማስከበሪ 10% አስይዘው ውል ለመፈራረም ፍቃደኛ የሆኑ፤
- ተጫራቾች ስለመልካም ስራ አፈጻጸማቸው ከአሁን በፊት የሂሳብ ምርመራ የኦዲት ግልጋሎት ከሰጡበት ተቋም ድርጅት የተጻፈላቸውን ማስረጃ የሚያቀርቡ፣
- ሂሳብ ምርመራው የሚያደርገው በድርጅቱ ዋና መ/ቤት በአማራ ክልል ደ/ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ የማሻ ከተማ መሆኑን አውቀው የሚሳተፍ፤
- ተጫራቾችን ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 150 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል ደ/ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ ማሻ ከተማ ከድርጅቱ ዋና መ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 1 ዘወትር በስራ ሰዓት ማግኘት ይችላሉ። የቀረበውን የጨረታ ሰነድ ታክስ ጨምሮ ዋጋ በመሙላት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡30 የሚከፈት ሲሆን 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆን በሚቀጥለው የሰራው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ የሚከፈት ይሆናል፤
- ተጫራቾች የበጀት አመቱን የኦዲት ስራ የሚከናወንበትን የስራ ዝርዝር እና በመጨረሻ የሚቀርቡት የኦዲት ሪፖርት ይዘት እንዲሁም የሚወስድባቸውን ጊዜ የሚያሳይ የድርጊት መረሃ ግብር /ማስኬጃ ውል /በማዘጋጀት ከንግድ ፍቃድ እና ጨረታ ሰነዱን ጋር በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጮችን ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0910584879/0911981886/ 0913974566/0905169830/መደወል ይችላሉ።
ስንቅ በጎ አድራጎት ድርጅት
