የኩራ ጅዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የ2018 ዓ.ም. የተለያዩ ቋሚ ዕቃዎች፣ አላቂ ዕቃዎች፣ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ ፈርኒቸሮች እንዲሁም የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የኩራ ጅዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የኩራ ጅዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የ2018 ዓ.ም. የተለያዩ ቋሚ ዕቃዎች፣ አላቂ ዕቃዎች፣ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ ፈርኒቸሮች እንዲሁም የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ ድርጅቶች መወዳደር ትችላላችሁ።
- ቅጽ 1. የፅህፈት መሳሪያዎች
- ቅጽ 2. የፅዳት ዕቃዎች
- ቅጽ 3. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
- ቅጽ 4. ፈርኒቸሮችን ለመጫረት የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-
- ተጫራቾች በጨረታ ለመካፈል ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ / VAT የሚቆርጡ/ እና TIN ለዚሁ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በሌላም በሚመለከታቸው ፈቃድ ሰጪ አካላት በአቅራቢነት የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው ተጫራቾች ብቻ መካፈል ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 100 በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- 15ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት የድርጅቱ ባለቤት ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታው ሳጥን ይከፈታል፡፡ እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ፍርድ ቤቱ ካቀረበው መስፈርት /standard/ በታች ማቅረብ አይቻልም።
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታ ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይቻልም።
- ፍርድ ቤቱ የሚያጫረታቸውን እቃዎች ብዛት እንደአስፈላጊነታቸው (25%) በመጨመር ወይም በመቀነስ ማዘዝ ይችላል፡፡
- ፍርድ ቤቱ የሚያጫርታቸውን ዕቃዎች ብዛት ለተከታታይ 6 ወራት ውል ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ይዋዋላል።
- የሚገዙ ዕቃዎች በተሠጠው እስፔስፊኬሽን መሠረት ተሟልተው ካልቀረቡና ማንኛውንም ዓይነት ስህተት ቢፈጸም ሀላፊነቱ የእቅራቢው ድርጅት ነው።
- የሚቀርቡትን ዕቃዎች አይነት /ናሙና/ ዘወትር በስራ ሰዓት መ/ቤታችን ድረስ ማምጣት ይችላሉ። ማንኛውም ናሙና አሪጅናል መሆን አለበት፡፡
- ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች አቅራቢው ድርጅት በራሱ ትራንስፖርት መ/ቤቱ ግምጃ ቤት ድረስ በማምጣት ገቢ ያደርጋል።
- በማንኛውም ተጫራች በጨረታው ተካፋይ ለመሆን ተመላሽ የሚሆን ብር 4000 /አራት ሺህ/ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ባኩራ ጅዳ ክፍለ ከተማ ባለ ባንክ ማስያዝ ይኖርበታል።
- አሸናፊዎች በሚገቡት ውል መሰረት ለመፈጸም ለውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተመሰከረለት ሲፒአ ወይም ካሽ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ለውል ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ወይም የተመሰከረለት ሲፒኦ ውሉ መፈጸሙ እስኪረጋገጥ ድረስ ይቆያል፡፡
- በአንድ ተጫራች በሌላው ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ በፍጹም አይቻልም።
- ፍ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ኩራ ጅዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት
ኩራ ጅዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት
