የአሶሳ ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ 2018 ዓ/ም ለሰራተኞች ደንብ ልብስ አገልግሎት የሚውል ሎት1 ጨርቅ ቴታሮን 6000 (ለወንዶች ሙሉ ልብስ እና ለሴቶች ጉርድና ኮት)፣ የቱታ/የጋዎን ነጭ ጨርቅ፣ አጭር የቆዳ ጫማ የሴቶች እና የወንዶች)፣ ሸሚዝ (የሴቶች እና የወንዶች)፣ ፕላስቲክ ቡትስ ጫማ፡ ለጽዳት ሰራተኞች እጅ ጓንት፣ አጭር ጉርድ ውስጥ ልብስ፣ ሎት 2 የደንብ ልብስ ስፌት የእጅ ዋጋ የወንዶች ሙሉ ልብስ ከነ-ገበር፣ የሴቶች ጉርድና ኮት፣ ጋምን፣ ሽርጥ ከነቆብ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
Asosa Agricultural TVET College (የአሶሳ ግብርና ቴክኒክ ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የአሶሳ ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ 2018 ዓ/ም ለሰራተኞች ደንብ ልብስ አገልግሎት የሚውል ሎት1 ጨርቅ ቴታሮን 6000 (ለወንዶች ሙሉ ልብስ እና ለሴቶች ጉርድና ኮት)፣ የቱታ/የጋዎን ነጭ ጨርቅ፣ አጭር የቆዳ ጫማ የሴቶች እና የወንዶች)፣ ሸሚዝ (የሴቶች እና የወንዶች)፣ ፕላስቲክ ቡትስ ጫማ፡ ለጽዳት ሰራተኞች እጅ ጓንት፣ አጭር ጉርድ ውስጥ ልብስ፣ ሎት 2 የደንብ ልብስ ስፌት የእጅ ዋጋ የወንዶች ሙሉ ልብስ ከነ-ገበር፣ የሴቶች ጉርድና ኮት፣ ጋምን፣ ሽርጥ ከነቆብ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት በጨረታው መሳተፍ ለምትፈልጉ ተጫራቾች፡-
- ተጫራቾች በዚህ ንግድ ሥራ ዘርፍ ለመስራት የሚያስችላችሁ ህጋዊ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የዘመኑ የ2017/2018 ዓ/ም ግብር የከፈሉ እና በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት (VAT) የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን በግልጽ የመወዳደሪያ ከተራ ቁጥር 1-3 የተዘረዘሩት ሠነዶቻችውን ኦሪጅናልና ፎቶ ኮፒን በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስታውቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እሰከ 15ኛው ተከታታይ ቀን 8፡00 ድረስ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን አሶሳ ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ ድረስ በማምጣት ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
- የእያንዳንዱ እታ ዋጋ የሚሞላው ኮሌጁ በሰጠው አስፔሲፊኬሽን ዝርዝር ላይ ብቻ ይሆናል፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ተከታታይ ቀን እስከ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 8:30 ሰዓት ላይ ጨረታው በግልጽ ይከፈታል፡፡ ቀኑ ቅዳሜ እሁድ በዓል ቀን ሳይ ከዋለ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ወይንም ለመለየት አሻሚ የሆነ ነገር መኖር የለበትም፣
- ሌሎች ተጫራች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፣
- ተጫራቾች የጨረታውን ሙሉ ዝርዝር የያዘ ሰነድ ብር 200 የማይመለስ በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከሰኞ እስከ አርብ ለተከታታይ 15ኛው ቀን አሶሳ ግብርና ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሴጅ ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ መግዛት ይቻላል፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 2 ፐርሰንት ከታወቀ ባንክ ጋራንቲ ወይንም ሲፒኦ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ከጨረታ ሰነድ ጋር በማስያዝ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ 2 ፐርሰንት ሲፒኦ ካላቀረበ ወይም ከ2 ፐርሰንት ያነሰ ከሆነ ከውድድሩ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይሰረዛል፣
- ኮሌጁ አሸናፊ ድርጅት የሚመርጠው በእያንዳንዱ ዕቃ ዝቅተኛ ዋጋ እንጂ በጠቅላላው ድምር ዋጋ አይደለም።
- አሸናፈዎች የውል ማስከበሪያ ያሸነፋበት 10% በማስያዝ ማሸነፉ ከተገለፀላቸው በ5 ቀናት ውስጥ ውል መግባት አለባቸው።
- አሸናፈዎች እቃውን የሚያስረከቡት ለሎት 1 ፣ ሎት 2 በአሶሳ ግ/ት/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ ውስጥ ባለው ንብረት ክፍል ይሆናል፣
- ስለጨረታው አጠቃላይ መረጃ ከጨረታ ሰነዱ እና ከተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡
- የጨረታ መዝጊያ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፣
- ተጫራቾች በጨረታው መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባይገኙ የጨረታ ሂደት አይስተጓጉልም፣
- ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተሰጠው ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- ፌስቡክ ገጽ Asosa Agricultural TVET College ወይም በሞባይል ስልክ ቁጥር 0911106356/0917176304/0924974707
የአሶሳ ግብርና ቴክኒክ ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ
