Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ሰርጢ ጤና ጣቢያ በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ ከዚህ በታች የተገለፁትን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ሰርጢ ጤና ጣቢያ


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ሰርጢ ጤና ጣቢያ በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ ከዚህ በታች የተገለፁትን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። የደንብ ልብስ፣ ህትመት፣ የጽዳት ዕቃ፣ የላብራቶሪ ሬኤጀንቶች፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የቤት ጥገና አገልግሎት እና ልዩ ልዩ እቃዎች ከህጋዊ አቅራቢዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ማሳሰቢያ

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው፤
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን እና የታደሰ መሆን አለበት እንዲሁም ከግዥ ኤጀንሲ online ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ሰርተፍኬት ማስያዝ አለባቸው፣
  3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት እቃ ናሙና በእስፔስፊኬሽን መሰረት ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ሳምፕል እና ለቋሚ እቃ ፎቶ ማቅረብ አለባቸው። እንዲሁም በእጃቸዉ ላይ የሚገኝ በተጠየቁ ሰዓት ወዲያው ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት የተቀመጠውን በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ብቻ ማስያዝ አለባቸው።
  5. በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፀው ሙሉ ዝርዝር ሁኔታ የጨረታው መመሪያ ሆኖ ችግሮች ካጋጠሙ በግዥው መመሪያ የሚዳኙ ይሆናል።
  6. ተጫራቾች የሞሉትን ሰነድ በፖስታ አሽገው ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ ብለው በመፃፍ የድርጅታቸውን ማህተም ፊርማ በማድረግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፣
  7. የውል ማስከበሪያ የግዥውን ግምታዊ ዋጋ 10% ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ብቻ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
  8. የወሰዱትን ሰነድ ዋና ዋና ቦታዎች ላይ እና ዋጋ የሞሉበት ሰነድ በመፈረም እና የድርጅታቸውን ማህተም በመምታት ሙሉ ሰነዱን ተመላሽ ማድረግ አለባቸው።
  9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ በዋለ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 412 ይከፈታል።
  11. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው አስር የስራ ቀናት ተከታታይ ቢሮ ቁጥር 412 በመቅረብ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ሰነድ መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
  12. የላብራቶሪ ሬኤጅንቶች ላይ የምትወዳደሩ የFDA /ከኢትዮጵያ ከመድኃኒት አቅራቢ ድርጀት የፍቃድ ሰርተፍኬት ማያያዝ አለባችሁ።
  13. ከጥቃቅን እና አነስተኛ ተጫራቾች ከተቋሙ በፅ/ቤት ኃላፊ የተፈረመ የድጋፍ ደብዳቤ እና አምራች ስለመሆናቸው ማረጋገጫ እና ስለሚያመርቱት ምርት ሰርተፍኬት ማምጣት አለባቸው።
  14. የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ወይም በካሽ መቅረብ ስላለበት ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሠረት ጨረታ ማስከበሪያ እንድታሲዙ እያሳሰብን ለጨረታ ማስከበሪያ የምታቀርቡት (የምታሰሩት) (CPO) ወይም በካሽ ብቻ ማስያዝ እንዳለባችሁ እና የምታስይዙትን በየሎቱ በዝርዝር እንደሚከተለው አስቀምጠናል።

በመሆኑም

  • 6211 - ደንብ ልብስ የሚወዳደር =90,000.00 ብር
  • 6212 - አላቂ የቢሮ እቃዎች የሚወዳደር = 50,000.00 ብር
  • 6213- ህትመት የሚወዳደር = 60,000.00 ብር
  • 6214 - የላብራቶሪ ሬኤጀንቶች ላይ የሚወዳደር = 40,000.00 ብር
  • 6218 - አላቂ የጽዳት እቃዎች የሚወዳደር =80,000.00 ብር
  • 6219 - ልዩ ልዩ እቃዎች የሚወዳደር 60,000.00 ብር
  • 6313 - ቋሚ እቃዎች የሚወዳደር 80,000.00 ብር
  • 6244 - የቤት ጥገና የሚወዳደር = 20,000.00 ብር
  • 6243 - ኤሌክትሮኒክስ ጥገና የሚወዳደር = 12,000 ብር

አድራሻ ፡- አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ በወረዳ 8 ደራርቱ ቱሉ ት/ቤት አጠገብ ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልከ ቁጥር /011-439-89-08 ይደውሉ።

ከአንድ በላይ ጨረታ የወጡ መደቦች ላይ ዋጋ የሚሞላ ተጫራች የሞላውን እቃ ድምር ሁሉም ላይ የሞላ ደግሞ የሁሉንም ድምር የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት።

 

በአቃ/ቃ/ክ/ከ/ጤ/ጽ/ቤት የሰርጢ ጤና ጣቢያ

 

Save Tender