Tender Detail

Tender Details


በኢሉአባቦራ ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር የዳሪሙ ወረዳ ቴ/ሙያ እና ትምህርት ሥልጠና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም የበጀት ዘመን ለስልጤና፤ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የዳሪሙ ወረዳ ቴ/ሙያ እና ትምህርት ስልጠና ኮሌጅ


የጨረታ ማስታወቂያ

በኢሉአባቦራ ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር የዳሪሙ ወረዳ ቴ/ሙያ እና ትምህርት ሥልጠና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም የበጀት ዘመን ለስልጤና፤ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት:-

  • የጽህፈት መሳሪያዎችና የዕዳት ዕቃዎች
  • የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
  • የቢሮ ዕቃዎች ወይም ፈርኒቸሮች
  • የደንብ ልብሶች
  • የግንባታ መሣሪያዎች
  • የተለያዩ ጎማዎች
  • የተለያዩ ሕትመቶች
  • የጋርሜንት ዕቃዎች ወይም ጨርቃ ጨርቆች
  • የግብርና መሣሪያዎች
  • የጸጉር መሥሪያ ዕቃዎች ወይም Hairdressing materials
  • በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

1. ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው::

2. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ግብር የከፈሉበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

3. የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4. የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተመሰከረ ቼክ ወይም ሲፒአ ከውድድር ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡

5. አሸናፊ ተጫራቾች ለመልካም ሥራ አፈፃፀም የጠቅላላ ዋጋውን 10%ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

6. ተጫራቶች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት የጨረታውን ሰነድ ከኢሉአባቦር ዞን ዳሪሙ ቴ/ሙያ እና ትምህርት ሥልጠና ኮሌጅ በመውሰድ ሁሉንም ሰነድ በሃምሳ ብር በመግዛት ዋጋውን ሞልተው ከገዙበት ቀን ጀምሮ እሰከ 5/2/2018 ዓ.ም ቀን ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ጽ/ቤት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በ6/2/2018 ዓ.ም እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

8. የጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ6/2/2018 ዓ.ም 8፡30 ሰዓት በግልፅ ይከፈታል፡፡

9. የዕቃው ማስረከቢያ ቦታ ዳሪሙ ቴ/ሙያ እና ትምህርት ሥልጠና ኮሌጅ ሆኖ ጠቅላላ ወጪ የሻጩ ግዴታ ናቸው፡፡

10. በሌላ ተጫራቾች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡

11. የዕቃው ብዛት ከውድድር በኋላ የሚገለፅ ይሆናል፡፡

12. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው::

ከተራ ቁጥር፡- 1-12 በተጠቀሰው መስፈርቶች ያልተስማማ በጨረታው መሳተፍ የለበትም፡፡

ስተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0474440346/0917850867 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡

የዳሪሙ ወረዳ ቴ/ሙ/ት/ሥልጠና ኮሌጅ

Save Tender