Tender Detail

Tender Details

  • Company Hibret Insurance Company S.C. (ሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ)
  • Address ቴዎድሮስ አደባባይ በሚገኘው ሕብረት ኢንሹራንስ ሕንፃ ዋና መ/ቤት 9ኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251111263434
  • Websitehttps://www.hibretinsurance.com/
  • Deadline09 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-10-09 00:00:00
  • Categories Land , House, Building And Warehouse

ሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሐል ከተማ ዉስጥ ከሪል እስቴት አልሚ ባለሕንፃዎች ላይ ለቢሮ አገልግሎት የሚዉልና የጋራ መገልገያ ጨምሮ ከ60-90 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ቤት ለቢሮ አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

Hibret Insurance Company S.C. (ሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ)


 

ሕብረት ኢንሹራንስ HIBRET INSURANCE

የጨረታ ቁጥር 25-26-015

ለቢሮ አገልግሎት የሚሆን የቤት ግዢ ጨረታ

 

ሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሐል ከተማ ዉስጥ ከሪል እስቴት አልሚ ባለሕንፃዎች ላይ ለቢሮ አገልግሎት የሚዉልና የጋራ መገልገያ ጨምሮ ከ60-90 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ቤት ለቢሮ አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።

  1. ተጫራቾች በሪል እስቴት የማልማት ሥራ መስክ ላይ መሰማራት የሚያስችል የታደሰ ንግድ ፍቃድ ተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ እና የታክስ ክፍያ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው።
  2. ተጫራቾች ለገነቡት ሕንፃ የይዞታ ማረጋገጫ ሕጋዊ ካርታ እንዲሁም ሕንፃው የተሰራበት የግንባታ ፍቃድ ማቅረብ አለባቸው።
  3. ተጫራቾች ሕንፃ ገንብተው ለመኖሪያ እና ለቢሮ አገልግሎት መሸጥ የሚያስችል ሪል እስቴት የማልማት መንግስታዊ ፍቃድ ያላቸው መሆን አለበት።
  4. ተጫራቾች ለመሸጥ የሚያቀርቡት ቢሮ የሚገኝበት ሕንፃ በአዲስ አበባ ከተማ ፒያሣ፣ ሜክሲኮ፣ ለገሃር፣ ሳርቤት፣ ቦሌ መድኃኒዓለም፣ ቦሌ መንገድ፣ መገናኛ፣ አራት ኪሎ እና ገርጂ በዋና መንገድ ዳር መሆን ይኖርበታል።
  5. ተጫራቾች ለሽያጭ ያቀረቡት ቢሮ ከምድር ቤት (ግራውንድ) ወለል እስከ 3ኛ ወለል ላይ ባሉ ቦታዎች ላይ መገኘት ይኖርበታል።
  6. ተጫራቾች ለመሸጥ የሚያቀርቡት ቢሮ ቢያንስ ለአንድ ቋሚ መኪና ማቆሚያ ሊኖረው ይገባል።
  7. ተጫራቾች ለመሸጥ የሚያቀርቡት ቢሮ የግል ወይም የጋራ መገልገያ መፀዳጃ ቤት ሊኖረው ይገባል።
  8. ተጫራቾች የቢሮውን ሽያጭ ካከናውኑ በኋላ የሸጡትን ቤት ስመ ንብረት ቢበዛ በ6 ወር ጊዜ ውስጥ በገዢ ስም የማዞር ግዴት አለባቸው።

በመሆኑም ከላይ የተዘረዘሩትን ተጫራቾች ስለ ጨረታዉ የሚያሟሉ ዝርዝር ሁኔታ የሚገልፀዉን ሰነድ ቴዎድሮስ አደባባይ በሚገኘው ሕብረት ኢንሹራንስ ሕንፃ ዋና መ/ቤት 9ኛ ፎቅ ላይ ካለው ከሰው ሃብትና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ከመስከረም 19 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ከጥዋቱ 2፡00 እስከ 11፡00 ድረስ በመውሰድ መሙላትና በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማሸግ በዚሁ ቢሮ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ መስከረም 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ድረስ በማስገባት መወዳደር ይችላሉ።

ጨረታው መስከረም 29 ቀን 2018 ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩባንያው በዋና መ/ቤት ሕንፃ 11ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘዉ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።

ኩባንያዉ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 25111 26 34 34 የውስጥ መስመር 207,190 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

 

Save Tender