Tender Detail

Tender Details

  • Company ተስፋ ድርጅት
  • Address አየር ጤና ሳሚ ካፌ ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0113482537
  • Website
  • Deadline09 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security50,000.00 (አምሣ ሺህ ብር)
  • opening date2025-10-09 00:00:00
  • Categories Agriculture And Farming , Food And Beverage

ተስፋ ድርጅት በሲቪል ማህበራት ኤጀንሲ የተመዘገበ ህጋዊ ድርጅት ሲሆን ለሚረዳቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ከዚህ በታች የተገለፀውን የጤፍ አይነት አቅራቢዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ተስፋ ድርጅት


 

የጤፍ ጨረታ ማስታወቂያ

 

ተስፋ ድርጅት በሲቪል ማህበራት ኤጀንሲ የተመዘገበ ህጋዊ ድርጅት ሲሆን በአገራችን በተለያዩ ክልሎች ማለትም በጋምቤላ፣ ቤንሻንጉል፣ በኦሮሚያ፤ በአማራና ሲዳማ ክልል እንዲሁም በአዲስ አበባ ባሉት ቅርንጫፎች በትምህርት፣ በሙያ ሥልጠና እና በተለያዩ የልማት ሥራዎች የኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅተኛ ለሆኑ ወገኖች አገልግሎት ይሰጣል። ስለሆነም ለሚረዳቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ከዚህ በታች የተገለፀውን የጤፍ አይነት አቅራቢዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

 

ተ.ቁ

አይነት

መለኪያ

ብዛት

ማስረከቢያ ቦታ

1

ሰርገኛ ጤፍ

ኩንታል

200

ተስፋ ድርጅት ደሴ ቅርንጫፍ

 

ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።

  1. የታደሰ የንግድ ምዝገባ ስርተፊኬት ያላቸው መሆን አለባቸው።
  2. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እንዲሁም ተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርቲፊኬት ያላቸው መሆን አለባቸው።
  3. የግብር መለያ ቁጥር (Tin No.) ሰርቲፊኬት ያለው።
  4. ተጫራቾች የሚያስገቧቸውን የዋጋ ሰነዶች የቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት ለየብቻ ወይም ሁለቱን የታሽጉ ፖስታዎች በአንድ ፓስታ በማሸግ ከነሳምፕሉ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 29 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀነ- 6:00 ድረስ ተስፋ ድርጅት ዋናው መሥሪያ ቤት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000.00 (አምሣ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ብቻ በድርጅቱ ስም አሰርቶ ከቴክኒካል ዶክመንቱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መስከረም 29 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀነ- 8.00 ሰዓት ይከፈታል።
  7. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም ከድርጅቱ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመግዛት በተዘጋጀው ፎርም ብቻ ዋጋ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  8. ተጫራጮቾች የሚያቅረቡት ዋጋ እስከ ማስረኪቢያ ቦታ ያለውን የትራንስፓርት ዋጋ ጭምር የያዘ መሆን አለበት።
  9. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡-

ተስፋ ድርጅት ዋናው መ/ቤት

አየር ጤና ሳሚ ካፌ ፊት ለፊት

ስልክ ቁጥር 0118 72 36 19

አዲስ አበባ

 

Save Tender