የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 002/2018
ለፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚውል
ሎት 1 የፅዳት ዕቃዎች
ሎት 2 የፅህፈት መሳሪያዎች
ሎት 3 የደንብ ልብስ በግልፅ ጨረታ በዘርፉ የተሰማሩና በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢ ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡-
-
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት ከሎት 1 እስከ ሎት 3 ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) ከፍለው ከድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 28 በመምጣት ማግኘት ይችላሉ፡፡
-
ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉና ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት እንዲሁም የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
-
ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ ቴክኒካልና ፋይናንሽያል ፖስታ ኮፒ እና ኦሪጅናል ለየብቻ በማዘጋጀትና በኢንቨሎፕ በማሸግ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 28 በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
-
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /Bid Bond/ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ቫትን ጨምሮ የጠቅላላ ዋጋውን 2% በፖስታ ለብቻ በማሸግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
-
ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት 1፣ 2 እና 3 ለሚያቀርቡት እቃ ሳምፕል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
-
ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር 28 ይከፈታል የመከፈቻው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በበዓል ላይ ከዋለ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ቦታ እና ሰዓት ይከፈታል፡፡
-
አገልግሎታችን ጨረታውን በከፊልም ይሁን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ አድራሻ፡- ከሜክሲኮ ወደ ልደታ ቤተክርስቲያን የሚወስደው መንገድ ላይ ፖሊስ ሆስፒታል ፊት ለፊት ነው፡፡ ለተጨማሪ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 0115-15-51-59
የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት
