Tender Detail

Tender Details


በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በአርሲ ዞን አሰላ ከተማ የሚገኘው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለሥልጠና እና ለቢሮዎች መገልገያ የሚውሉ ለተለያዩ ዕቃዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አርሲ/አሰላ


                                                                         የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ 

 

 

በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በአርሲ ዞን አሰላ ከተማ የሚገኘው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለሥልጠና እና ለቢሮዎች መገልገያ የሚውሉ ለተለያዩ ዕቃዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የጨረታ ጥቅሎች እንደ ሥራ ፈቃዳችሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመግዛት የምትሸጡበትን ዋጋ ሞልታችሁ እንድታቀርቡ ተጋብዛችኋል፡፡ 

የጨረታ ሎት ቁጥር 01 የብረታ ብረት ዕቃዎች፡፡ 

* የጨረታ ሎት ቁጥር 02-1 የሕንጻ መሣሪያዎች ፡፡ 

* የጨረታ ሎት ቁጥር 02-2 ቧንቧ መሣሪያዎች እና የሳኒተሪ እቃዎች ፡፡

* የጨረታ ሎት ቁጥር 03 ኤሌክትሪክ ዕቃዎች፡፡

* የጨረታ ሎት ቁጥር 04 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ፡፡ 

* የጨረታ ሎት ቁጥር 05 አውቶሞቲቭ ዕቃዎችና የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች ፡፡ 

* የጨረታ ሎት ቁጥር06 የጋርመንት እቃዎች 

* የጨረታ ሎት ቁጥር 07 የእፅዋት እና የተፈጥሮ ሀብት ዕቃዎች፡፡ 

* የጨረታ ሎት ቁጥር 08 የእንስሳት ህክምና እና የእንስሳት ዕርባታ ዕቃዎች፡፡ 

* የጨረታ ሎት ቁጥር 10 ኮምፒውተር ዕቃዎች፡፡ 

  1. በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ 

  2. ተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም TOT የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ 

  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ 

  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ዋናውን እና ኮፒ በማቅረብ ዕቃዎችን በራሳቸው ትራንስፖርት ለኮሌጁ የሚያቀርቡበትን ዋጋ ኮሌጁ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ በብር 500 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመግዛት መሙላት ይችላሉ፡፡ 

  5. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኮሌጁ የግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡ 

  6.  ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን አንስቶ በአስራ ስድስተኛው ተከታታይ የሥራ ቀን ከቀኑ በ8፡oo በኮሌጁ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 

  7.  አስራ ስድስተኛው ተከታታይ ቀን በካላንደር ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ቦታ እና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 

  8. የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን አንስቶ በ5 ቀናት ውስጥ ውል በመግባት ግብአቶችን በራሱ ትራንስፖርት ኮሌጁ ድረስ ማምጣት አለበት፡፡ 

  9.  ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

  10. ተጫራቾች ለበለጠ መረጃ 0223314901 ወይም 0223312252/51 መደወል ይችላሉ፡፡

 

                                    አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አርሲ/አሰላ

Save Tender