Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አቃቂ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ
  • Address አቃቂ ልዩ ስሙ የድሮው ምክር ቤት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የአቃቂ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-8-42-03-30
  • Website
  • Deadline10 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Securityለሎት 1 የብር 92,000 (ዘጠና ሁለት ሺህ ብር)፣  2 ለሎት 2 የብር 13,309 (አስራ ሶስት ሺህ ሶስት መቶ ዘጠኝ ብር)፣ 3 ለሎት 3 የብር 92,977 (ዘጠና ሁለት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባ ሰባት ብር)፣ 4. ለሎት 4 የብር 16,373 (አስራ ስድስት ሺህ ሶስት መቶ ሰባ ሶስት ብር)
  • opening date2025-10-10 00:00:00
  • Categories Office Supplies And Services , Textile, Garment & Leather , Cleaning And Janitorial Equipment , Materials , Stationery Materials

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የአቃቂ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አቃቂ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ


 

የግዥ መለያ ቁጥር አ/ጤ/ጣ 001/2018 ዓ.ም የጨረታ ቁጥር 001/2018

 

1. ሎት1 የደንብ ልብስ፣ 2 ሎት 2 የጽህፈትና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ 3 ሎት 3 አላቂ የጽዳት ዕቃዎች፣ 4 ሎት 4 ልዩ ልዩ ዕቃዎች ከዚህ በላይ በተዘረዘሩት ግዥዎች መወዳደር የምትፈልጉ አቅራቢዎች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባችኋል።

  1. ለተጠቀሱት ዕቃዎች ግዥ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከአቃቂ ጤና ጣቢያ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 30 በአካል በመቅረብ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
  2. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉና ለሚያቀርቡት ዕቃ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ።
  3. ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች የአቅራቢነት ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ለተወዳደሩበት መደብ 1 ለሎት 1 የብር 92,000 (ዘጠና ሁለት ሺህ ብር)፣  2 ለሎት 2 የብር 13,309 (አስራ ሶስት ሺህ ሶስት መቶ ዘጠኝ ብር)፣ 3 ለሎት 3 የብር 92,977 (ዘጠና ሁለት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባ ሰባት ብር)፣ 4. ለሎት 4 የብር 16,373 (አስራ ስድስት ሺህ ሶስት መቶ ሰባ ሶስት ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለትና ተመላሽ የሚሆን ዋስትና ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
  6. ተጫራቾች በሚወስዱት የመ/ቤቱ ሰነድ ላይ ቫትን ያካተተ ዋጋ በመሙላት ሙሉ ሠነዱ መመለስ አለበት።
  7. በጤና ተቋሙ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ስፔስፊኬሽን በመሰረዝ ማስተካከል አይቻልም።
  8. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ በግልጽ በመሙላት የድርጅቱን ማህተም በሠነዱ ላይ በመምታት አሪጅናሉንና ኮፒውን በተለያ ፖስታ በማድረግ ሁለቱንም ፖስታዎች በአንድነት በኤልቨሎፕ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት በጤና ጣቢያው ቢሮ ቁጥር 32 ዘወትር በስራ ሠዓት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
  9. ጨረታው በ11ኛው ቀን ጠዋት 3፡30 (ሶስት ሰዓት ተኩል) ተዘግቶ በዚያው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 (አራት ሰዓት) ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 (አራት ሰዓት) ላይ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጤና ጣቢያው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
  10.  የጨረታ አሽናፊ የሆነ ተወዳዳሪ የውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የሚያሲዝ ይሆናል።
  11.  ተጫራቾች በሁሉም በሚጫረቱበት ዕቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ ከ1 (አንድ) ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በእጅ የማይያዙ ናሙናዎችን ግልፅ በሆነ ፎቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።በሚያቀርቧቸው ናሙናዎች ላይ ከአምራች ድርጅቱ በስተቀር ሌላ ምንም ዓይነት ምልክት ወይም የተጫራቹ ማህተም የተደረገበት ከሆነ ተቀባይነት አይኖረውም።
  12.  በካሬ የሚለኩ ግዥዎች ላይ ተጫራቾች ቦታው ላይ በመገኘት መለካት ይኖርባቸዋል።
  13.  የተሰረዘ ፣ የተደለዘ እና ግልፅነት የሌለው የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይሆናል።
  14.  መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  15.  ጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች ከተቋሙ የድጋፍ ደብዳቤ እና የአምራችነት ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

አድራሻ፡- አቃቂ ልዩ ስሙ የድሮው ምክር ቤት

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የአቃቂ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ

ስልክ ቁጥር 011-8-42-03-30

 

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የአቃቂ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ

Save Tender