በቦሌ ክከተማ ወረዳ 01 ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን በ 2018 ዓ.ም በጀት አመት የእቅድ ማስፈፀሚያ የሚውሉ የተለያዩ አገልግሎት ግዥ ከዚህ በታች በተዘረዘረው ሎት በ1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ፋይናንስ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በጨረታ ቁጥር 001/2018 ዓ.ም
በቦሌ ክከተማ ወረዳ 01 ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን በ 2018 ዓ.ም በጀት አመት የእቅድ ማስፈፀሚያ የሚውሉ የተለያዩ አገልግሎት ግዥ ከዚህ በታች በተዘረዘረው ሎት በ1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ሎት 1 የጽሕፈት መሳሪያዎች ሎት 2 የፅዳት ዕቃዎች ሎት 3 የደንብ ልብስ
ስለዚህ መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች ቀርበው ሰነድ ገዝተው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል የዘመኑ ግብር የገበረ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ የተጫራቾች የምስክር ወረቀት ያላቸው ተጫራቾች እያንዳንዱ የሚወዳደሩበት ጨረታው የአቃውን ዝርዝር ሰነዱን ላይ ያለውን ብቻ መሰረት ማድረግ ይኖርባችዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበርያ በእያንዳንዱ ሎት ሎት 1) 20,000 ብር (ሃያ ሺ ብር) ሎት 2) 20,000 ብር (ሃያ ሺ ብር) ሎት 3) 20,000 ብር (ሃያ ሺ ብር) ከላይ የተቀመጠው የማስከበርያ ብር C.P.O ብቻ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሲያስገቡ የሚጫረተባቸውን እቃዎች ሳምፐል (ናሙና) ማቅረብ አለባቸዉ ከሎት የጨረታ ማስከበርያ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ለአንድ ጨረታ ሰነድ በመክፈል በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 0 ፋይናንስ /ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ መውሰድ ይችላል፡፡
- የጨረታ አሸናፈዎች ያሸነፉበት እቃዎችን በራሳቸው ትራንስፖርት ማቅረብ አለባቸው።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ሰነድ ውስጥ መ/ቤቱ ከጠቀሳቸው የእቃዎች ዝርዝር ውጪ ያስገቡ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ ይሆናሉ።
- የጨረታ አሸናፈዎች ያሸንፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው ዋጋው ጸንቶ የሚቆይበት አሸናፈው ከተለየበት አንስቶ ለ60 ቀናት ይሆናል፡፡
- ለእያንዳንዱ ለተወዳደሩበት በየሎቱ CPO ማስያዝ አለባችሁ ጥቅል CPO ካስገቡ ከጨረታ ውጭ ይሆናሉ፡፡
- በጥቃቅን የተደራጁ ከሆነ በሚያመርቱት ምርት ከሆነ ጨረታ ሰነድ በነጻ የሚወስዱ ይሆናል በማያመርቱ ምርት ላይ ሰነድ የሚገዙ ይሆናል።
- በጨረታ ሂደት ላይ ለማሳሳትና የማጭብርበር ስራ ላይ የሚሳተፉ ተጫራቾች ህጉ በሚያዘው በኢትዮጵያ ህግ የሚዳኝ ይሆናል።
- ለቋሚ እቃዎች ናሙና ለማይቀርብላቸው የእቃዎቹ አስፔፊኬሽን ከኦርጅናል ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ፖስታው ኮፒና ኦርጅናል በማሸግ ማስገባት አለባቸው። CPO ውን ኦርጅናሉን ሰነድ ላይ ማያያዝ አለበት ኮፒ ላይ ከተደረገ ከጨረታው ላይ ተሳታፊ አይሆኑም
- ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ ቫትን የጨመረ መሆን አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታው አፈጻጸም ሂደት ላይ ቅሬታ ቢኖረው, በ5 የስራ ቀናቶች ውስጥ ቅሬታ ማስገባት ይችላሉ። በ5ኛው ቀን ቅሬታ ማቅረብ አይችሉም፡፡
- ለጨረታ የቀረቡትን የእቃ ናሙናዎች ውጤት በተገለጸ በ0 ቀናት ውስጥ እቃዎችን መውሰድ አለባችሁ ይህ ባይሆን እቃዎቹ ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ይሆናል፡፡
- ጨረታውም አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ 10 የስራ ቀናቶች የሚቆይ ይሆናል 10ኛ ቀን ላይ 11፡00 ሰዓት ላይ የሚዘጋ ይሆናል በ11ኛው ቀን ሰነድ ማስገባት አይቻልም በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ሲሆን ቀኑ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ተጫራቾች ወይም ወኪሎች ቢኖሩም ባይኖሩም የሚከፈት ይሆናል ፡፡
- በበጀት ዓመቱ ሙሉውን ዓመት የዋጋ ማስተካከያ የማናደርግ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ቦሌ ወረዳ 0፣ ፋይናንስ ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ የግዥ ቡድን መሪ መጠየቅ ይቻላል።
አድራሻ፡- ቦሌ ሚካኤል ከጉምሩክ ወረድ ብሎ ኮንደሚኒየም ጀርባ ወረዳ 01 አስተዳደር ጽ/ቤት
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0118 16 02 11 ደውለው ይጠይቁ።
በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ፋይናንስ ጽ/ቤት
