Tender Detail

Tender Details


በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጌዴኦ ዞን ቡሌ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ለተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤት የጽሕፈት መሳሪያ ምድብ 1.  እስቴሽነሪ፣ ምድብ 2. የጽዳት ዕቃዎች፣ ምድብ 3. ኤሌክትሮኒክስ፣ ምድብ 4 ፈርኒቸሪ፣ ብቁ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዴኦ ዞን የቡሌ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጌዴኦ ዞን ቡሌ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ለተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤት የጽሕፈት መሳሪያ ምድብ 1.  እስቴሽነሪ፣ ምድብ 2. የጽዳት ዕቃዎች፣ ምድብ 3. ኤሌክትሮኒክስ፣ ምድብ 4 ፈርኒቸሪ፣ ብቁ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው/ያላት፤
  2. የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው ያላት፤
  3. የግብር ከፋይነት ቲን ቁጥር ያለው/ያላት፤
  4. ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ወቅታዊ የግብር ክፍያ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል/ትችል፤
  5. የቫት የምዝገባ ሰርተፊኬት ያለው/ያላት፤
  6. የአቅራቢዎች ስም ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው የሚገልጽ ማስረጃና ሌሎች ሰነዶችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች በጽ/ቤቱ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 400.00 (አራት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ ከጽ/ቤቱ ግዥ ኬዝ ቲም ቢሮ ቁጥር 3 መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ብቻ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በሲፒኦ (CPO) በቡሌ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ስም አሰርተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በታሸገ ፖስታ የዋጋና ቴከኒካል የጨረታ ሰነድ ማስገባት አለባቸው፡፡ ነገር ግን ጨረታ በሚከፈትበት ቀን ዘግይቶ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  9. የጨረታ ሰነድ ለ21 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ማቅረቢያ ጊዜው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ በ22 ቀን ጨረታው ስለሚከፈት የጨረታ አከፋፈቱን ስነ-ስርዓት መከታተል የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቡሌ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ግዥ ኬዝ ቲም ቢሮ ቁጥር 3 በ4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
  10. የጨረታው ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ዕለት ጀምሮ ለ30 ቀናት ብቻ ይሆናል፡፡
  11. ተጫራቾች የቴክኒካልና ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዶችን ለእያንዳንዳቸው አንድ ኦሪጅናል እና አንድ ኮፒ የጨረታ ሰነድ ማቅረብ አለባቸው።
  12. በተጫራቾች ተሞልተው የሚቀርቡ የመወዳደሪያ ሀሳብ ደጋፊ ሰነዶች በግልጽና በጥራት መግለጽ አለባቸው፡፡
  13. በተጫራቾች ተሞልተው የሚቀርቡ የመወዳደሪያ ሀሳብ እና ሌሎችም ተጨማሪ ማረጋገጫዎች በሚመለከተው ኃላፊ ፊርማና ማህተም ካልተደረገባቸው የቀረበው የመወዳደሪያ ሀሳብ ሊሰረዝ ይችላል፡፡
  14. አሸናፊው ተጫራች የውሉን አስር ፐርሰንት (10%) የአፈጻጸም ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  15. አሸናፊ ድርጅት ወይም ግለሰብ ያሸነፈበትን ዕቃ ቡሌ ፋይናንስ ጽ/ቤት ማቅረብ የሚችል/ትችል፡፡
  16. አሸናፊ ድርጅት ወይም ግለሰብ ያሸነፈውን ዕቃ ጥራት ለመለየት ናሙና ማቅረብ የሚችል/ትችል፡፡
  17. ጽ/ቤታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  18. በጨረታ ላይ ለሚነሱ ማንኛውም ጥያቄዎች በጽ/ቤታችን አድራሻ በኩል ምላሽ ማግኘት ይቻላል፡፡

 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዴኦ ዞን የቡሌ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender