Tender Detail

Tender Details

  • Company Robe College of Teachers Education (የሮቤ መምህራን ኮሌጅ)
  • Address ባሌ ሮቤ ከተማ ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0913223605
  • Websitehttps://www.rcte.edu.et/
  • Deadline17 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Security20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር)
  • opening date2025-10-17 00:00:00
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

የሮቤ መምህራን ኮሌጅ በሮቤ ከተማ ሮቤ መምህራን ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ ያሉትን ለንግድ አገልግሎት የሚውሉ ቤቶችን በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

Robe College of Teachers Education (የሮቤ መምህራን ኮሌጅ)


 

የቤት ኪራይ ጨረታ የጨረታ ቁጥር KBR.2/2018

 

የሮቤ መምህራን ኮሌጅ በሮቤ ከተማ ሮቤ መምህራን ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ ያሉትን ለንግድ አገልግሎት የሚውሉ ቤቶችን በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው መወዳደር ወይም መሳተፍ የሚፈልግ ድርጅት ወይም ግለሰብ፡-

  1. በጨረታ መወዳደር (መሳተፍ) የሚፈልግ ድርጅት ወይም ግለሰብ የጨረታ ሰነድ ከሮቤ መምህራን ኮሌጅ በመግዛት መሳተፍ ይችላል፡፡
  2. የጨረታ ሳጥኑ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ይሆናል፡፡
  3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የአንድ ካሬ ዋጋ በክፍሉ ካሬ ስፋት አባዝቶ የጠቅላላውን ካሬ የአንድ ወር ዋጋ መሙላት አለባቸው።
  4. ተጫራቹ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ ከሆነ ከተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) በፊት ያለውን ዋጋ መሙላት አለበት። በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታውቂያ ከወጣበት የስራ ቀን ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) ብቻ በሲንቄ ባንከ የሂሳብ ቁጥር 10729252112114 በመክፈል የከፈሉበትን የባንክ ደረሰኝ (Bank Deposit Slip) በመያዝ ከሮቤ መምህራን ኮሌጅ እቅድ፣ ግዥ፥ ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን ተወዳድሮ ካሸነፈ ያሸነፈበትን ዋጋ የሶስት ወር በአንድ ግዜ የሚከፍል ይሆናል፡፡
  7. ተጫራቹ ለጨረታ ማስከበሪያ 20,000.00 (ሃያ ሺህ) ብር የያዘ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ብቻ ከአሪጅናል የጨረታ ሰነድ ጋር በፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።
  8. ኮሌጁ ለማያከራያቸው (ማከራየት ለማይፈልጋቸው) የንግድ ዘርፎች ስላሉት ተጫራቾች ከጨረታው ሰነድ ጋር የተያያዘውን መመሪያ በማንበብ ተገንዝቦ መወዳደር አለባቸው።
  9. በእያንዳንዱ ሰነድ እና የታሸገ ፖስታ ላይ የድርጅቱን ስም እና ማህተም ወይም ግለሰብ ከሆነ የግለሰቡን ሙሉ ስም፣ፊርማ እና ስልክ ቁጥር በመፃፍ ማስገባት አለበት፡፡
  10. የጨረታው መወዳደሪያ ሰነድ በሁለት በታሸገ ፖስታ ኦሪጅናል እና በማይከፈት ኮፒ ሆኖ በፖስታው ላይ ኦሪጅናል እና ኮፒው በጽሁፍ ተለይቶ መቅረብ አለበት፡፡
  11. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት የስራ ቀን አንስቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት በሮቤ መምህራን ኮሌጅ እቅድ፣ ግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ በማስገባት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጥዋቱ 3:45 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
  12. ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ከአምስተኛው ቀን በኋላ ከ6ኛው ቀን ጀምሮ በአምስት የሥራ ቀናት ውስጥ በአካል በመቅረብ ውል መፈራረም አለባቸው፡፡
  13. ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0913223605/0930292418/0930292419 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

የሮቤ መምህራን ኮሌጅ

 

Save Tender