Tender Detail

Tender Details


በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ነገሮች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


 

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ 1ኛ/ የመኪና ጎማና ከለመዳሪ 15,000 ብር 2ኛ/ ህትመት 6,000 ብር 3ኛ/ የደን የዛፍ ዘር 2,000 ብር 4ኛ/ የስፖርት ትጥቅ እና ማቴሪያሎች 8,000 ብር 5ኛ/ የመኪና መለዋወጫ እቃ 20,000 6ኛ/ ቋሚ የቢሮ እቃዎች 4,000 ብር 7ኛ/ የጽዳት እቃ 2,000 ብር 8ኛ/ የግንባታ እቃ 10,000 ብር 9ኛ/ የውሃ እቃ 10,000 ብር በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን) እንዲሁም በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ድምር ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው የነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ሞልተው ኮፒና ኦርጅናል ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የጠቅላላ ዋጋ በዝርዝር ተሞልቶ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከላይ በተዘረዘረው ሎት የገንዘብ መጠን የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ ሲ.ፒ.ኦ /C.P.O/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር አፍ ክሬዲት ወይም በጥሬ ገንዘብ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቹ በዋጋ መሙያ ሰነድ ላይ ስም ፊርማና ማህተም በማድረግ በታሸገ ፖስታ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛ ቀን 3፡30 ድረስ በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለጨረታ በተዘጋጀ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. የጨረታ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ዕቃውን በሚ/ወ/ወ/ሴክተር መ/ቤቶች ባሉት ንብረት ክፍል ውስጥ ማድረስ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. የጨረታ ውድድሩ እንደአስፈላጊነቱ በነጠላ ዋጋ ወይም በሎት ሊሆን ይችላል፡፡
  8. ጨረታው ተጫራቾች በአካል ሆነ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባልተገኙበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡00 በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 18 ይከፈታል።  የመክፈቻ ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ላይ የጨረታ ሰነድ የመጨረሻ ማስገቢያ ከጠዋቱ 3፡30 ሆኖ ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ጨረታው ይከፈታል፡፡
  9. ማሳሰቢያ፡ ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን የስፖርት ትጥቅና ማቴሪያሎች ጥራት ያለው መሆኑን ለማረጋገጥ ናሙና ሳምፕል/ ማቅረብ አለባቸው።
  10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ ስ/ቁ 0111170171 ወይም 09 13 57 44 40 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

Save Tender