Tender Detail

Tender Details

  • Deadline14 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Security2%
  • opening date2025-10-14 00:00:00
  • Categories Cleaning & Janitorial

በደቡብ ወሎ ዞን ቦረና ወረዳ የመካነ ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል የፅዳት አገልግሎት ስራ አውት ሶርስ በማድረግ ለአንድ አመት ቆይታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማፀዳት ይፈልጋል፡፡


 

ለ3ኛ ጊዜ የወጣ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በደቡብ ወሎ ዞን ቦረና ወረዳ የመካነ ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል የፅዳት አገልግሎት ስራ አውት ሶርስ በማድረግ ለአንድ አመት ቆይታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማፀዳት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች በዝርዝር የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟላ መወዳደር ይችላል፡፡

  1. በመ/ሰ/ጠ/ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ የሚገኘውን እና አሁን በክልሉ በኩል እየተገነባ ያለው የማስፋፊያ ግንባታ የአገልግሎት መስጫ ክፍሎችና የቅጥር ግቢውን ንፅህና የሚጠብቅና የሚያፀዳ፡፡
  2. በጥቃቅን ለተደራጁ ኢንተርፕራይዝ አነስተኛ ህግ በሚያዘው መሰረት የተደራጀና መረጃ ማቅረብ የሚችል በመመሪያው መሰረት ይፈጸማል።
  3. ህጋዊ የንግደ ፍቃድ ያለውና በዘመኑ የታደለ መሆኑን የሚገልፅ መረጃ ማቅረብ የሚችል።
  4. ሆስፒታሉ በሚፈልገው መሰረት የተመረጠውን ክለርና ስፌት የደንብ ልብስ በስራ ሰአት በራሱ ወጭ አሟልቶ መልበስ የሚችል፡፡
  5. ጨረታው የሚከናወነው በሎት ነው፡፡
  6. ማኛውንም የጽዳት ዕቃዎች ለምሳሌ፡- በረኪና፣ ኦሞ፣ ላርጎ፣ ቪም፣ ድቶል፣ የፕላስቲክ መጥረጊያ መወልወያ እና ባልድና ፎጣ በራሱ ወጭ አሟልቶ ማጽዳት የሚችል።
  7. በጽዳት ስራ ላይ የሠራተኞች ብዛት 12 የሚሆንና ቅዳሜ እሁድ የህዝብ በአላት እና የአዘቦት ቀን በ24 ሰአት ውስጥ በጽዳት ስራ ላይ መገኘት አለባቸው፡፡
  8. የመጽዳጃ ቤቶች ንጽህና በመጠበቅ የሽንት ቤት መርዝ በመጠቀም መፀዳጃ ቤቶች ሽታ አልባ መደረግ አለባቸው፡፡
  9. የበረኪና አንድ ለዘጠኝ ውህደትን በመጠቀም የአገልግሎት መስጫ ክፍሎችን በመወልወል ንፅህናቸውን የሚጠብቅ፡፡
  10. አሸናፊው ተጫራች (ማህበሩ) በጽዳት ወቅት በየአገልግሎት መስጫ ክፍሎች የሚገኙትን ንብረቶች የጽዳት ሠራተኛው በእንዝላልነትና በግደለሽነት ምክንያት ለጠፋ /ለሚጠፋ/ ሠነዶች ቋሚና አላቂ እቃዎች የመንግስት ሀብትና ንብረት የሚከፍልና በህግ የመጠየቅ ግዴታ አለበት፡፡
  11. በሆስፒታሉ ህግና ደንብ መሰረት ተገዥ የሆነና ሌሎች ከጽዳት ጋር የተያያዙ ስራዎችን የሚሰጠውን ማንኛውንም ተግባር ተቀብሎ መፈፀም የሚችል።
  12. ማህበሩ መድቦ በሚያሰራው የጽዳት ሠራኞች የሚፈጠር ማንኛውንም ችግር ማህበሩ በህግ ተጠያቂ ይሆናል።
  13. በወር ለአገልግሎትና ለጽዳት እቃዎች ግዥ መጠየቂያ ደመወዝን ጨምሮ ሊከፍለው የሚችለውን ገንዘብ መጠን በኢትዮጵያ ብር ጥቅል ድምር በተዘጋጀው የመወዳደሪያ ሰነድ በወር እና በአመት በሚለው ጨረታ ሰነድ ላይ በትክክል መሙላት አለበት።
  14. ተወዳዳዎች የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ ብር 100 /መቶ ብር/ በመክፈል ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከመ/ሠ/ጠ/ሆ/ዋና ገንዘብ ያዥ መግዛት ይችላሉ፡፡
  15. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታ ሰነዱ ከመከፈቱ በፊት የጨረታ ማስከበሪያ 2% በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ ሲፒአ ወይም በጥሬ ገንዘብ በሞደል 85 ማሲያዝ አለባቸው፡፡
  16. በሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡ በተጨማሪም በተለያዩ እስኪብርቶ ጽፎ ማቅረብ የለበትም።
  17. ማንኛውም ተጫራች የሚጫረትበትን ዋጋ በተዘጋጀው ሠነድ ላይ በመሙላት በደንብ በታሸገ ፖስታ መካነ ሰላም ጠቅላላ ሆስፒታል ዘወትር በስራ ሰአት ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ዘወትር ተከታታይ 16 የስራ ቀናት በአየር ላይ ይውላል፡፡ የጫረታ ሰነዱ ዘወትር በስራ ሰአት ከግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሃደት ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላል፡፡ ጨረታው በ16ኛውቀን ከቀኑ 8፡00 ሰአት ይዘጋል። ቅዳሜ እና እሁድ (በአል) ላይ ከዋለ በቀጣይ ስራ ቀን ይከፈታል።
  18. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ከሰአት ጨረታው ይከፈታል፡፡
  19. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጫረታውን ሙሉ በሙሉ /በከፊል/ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  20. ጨረታውን መሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው መረጃ ከፈለጉ ከግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0923747044/0934370254/0914344306/ 0914334565 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል።

 

የመካነ-ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል

 

Save Tender