ቦሌ ማተሚያ ኃየተ.የግ.ማህበር ሎት 1 ለህትመት የሚሆኑ የተለያዩ ቀለሞች ሎት 2. የተለያዩ የጽዳት መጠቀሚያ ቁሳቁስ ሎት 3. የተለያዩ የስቴሽነሪ እቃዎችና የጽህፈት መሳሪያዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ቦሌ ማተሚያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር
የሀገር ውስጥ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
ቦሌ ማተሚያ ኃየተ.የግ.ማህበር፡- ሎት 1 ለህትመት የሚሆኑ የተለያዩ ቀለሞች ሎት 2. የተለያዩ የጽዳት መጠቀሚያ ቁሳቁስ ሎት 3. የተለያዩ የስቴሽነሪ እቃዎችና የጽህፈት መሳሪያዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት፣ የንግድ ሰርቲፊኬት እና ሌሎችም የህጋዊነት ማረጋገጫ ሰነዶችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በቅድሚያ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ/ ቢሮ ቁጥር 101 በመክፈል ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ድረስ ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ በሚገኘው ቢሮአችን መግዛት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የዋጋቸውን 2%፣ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ቴክኒካል እና ፋይናንሺል ሰነዶችን በአንድ ፖስታ አሽገው ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ግዥ ክፍል በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ያስገባሉ።
- ተጫራቾች ለጥራት ሙከራ ይሆን ዘንድ ከሚጫረቱበት አይነት ናሙና /ሳምፕል/ ከሰነዶቻቸው ጋር አብሮ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው 15ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በ3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማህበሩ የስብሰባ አዳራሽ /የግዢ ክፍል/ ይከፈታል።
- ድርጅቱ ሌላ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ-
ቦሌ ማተሚያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ስልክ ቁጥር …….. 01115 15 50 05/0115 51 88 72
ፋክስ …….. 0115 51 86 96
ፖ.ሳ.ቁ …….. 2365
ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ
አዲስ አበባ
