Tender Detail

Tender Details


በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ት/ጽ/ቤት የቤተልሔም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የጽሕፈት መሣሪያዎች የፅዳት ዕቃዎች፣ ቋሚ ዕቃዎች የደንብ ልብስ፣ የላብራቶሪ እቃዎች፣ ህትመት፣ የኤሌትሮኒከስ ጥገናዎች እና የደንብ ልብስ ስፌት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ት/ጽ/ቤት


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/18

በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ት/ጽ/ቤት የቤተልሔም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የጽሕፈት መሣሪያዎች የፅዳት ዕቃዎች፣ ቋሚ ዕቃዎች የደንብ ልብስ፣ የላብራቶሪ እቃዎች፣ ህትመት፣ የኤሌትሮኒከስ ጥገናዎች እና የደንብ ልብስ ስፌት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፤

በመሆኑም:-

1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፍቃድ፤ በመንግሥት ግዢ ዕቃ አቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምስከር ወረቀትና የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ እና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

2. የጨረታ ሰነዱ በሁለት ፖስታዎች ዋና /original እና ቅጂ /copy/ ኤንቬሎፕ ታሽጎ በጨረታ ሣጥን ውስጥ የጨረታው ማስረከቢያ ሰዓት ከመድረሱ በፊት በቤተልሔም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ክፍል መግባት ይኖርበታል፡፡

3. በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩ እቃዎች ናሙና (ሳምፕል)ማቅረብ ይኖርባችኋል ናሙና ለማቅረብ የማይቻሉ እቃዎች በፎቶ ማቅረብ ወይም የመሥሪያቤቱ ድርጅቱ ድረስ ለሚልካቸው ኮሚቴዎች ተፈላጊ እቃዎችን ማሳየት ይኖርባኋል፡፡

4. እያንዳንዱ ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ በ cpo ከዋናው (original) የጨረታ ሠነድ ውስጥ አድርጎ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

5. ለደንብ ልብስ ስፌት፣ ህትመት እና ለኤሌክትሮኒከስ ጥገና ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር) በcpo ከዋናው (original) የጨረታ ሠነድ ውስጥ አድርጎ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

6. ተወዳዳሪዎች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት መሥሪያ ቤታችን በግንባር በመገኘት የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በፋይናንስ ክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡

7. ጨረታው ማስታወቂያ በወጣ በ11ኛው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡

8. የጨረታ ሠነድ መቀበያ ሰዓት ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የመጫረቻ ሠነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

9. መሥሪያ ቤቱ ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈረሙ በፊት በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ መጨመር ወይም መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በአሸናፊው ተጫራች የቀረበው በውድድር የተገኘው ዋጋ ሳይቀየርእስከ 20 /ሃያ በመቶ) መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡

10. በጨረታው አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ድርጅት የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላው የእቃ ዋጋ 10% /አስር በመቶ/ ያህል በCPO ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሥሪያ ቤታችን ስም ማስያዝ ይኖርበታል፡፡

11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ቤተልሔም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት

አድራሻ-ጊዮርጊስ አ.አ ፖሊስ ኮሚሽን ፊት ለፊት

ስልክ:- 0111114800

ጌት የቤተልሔም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት

በአራዳ ክፍለ‐ከተማ ወረዳ 05 ት/ጽ/ቤት የቤተልሄም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት

Save Tender