በኦሮሚያ ከልል ጅማ ዞን የሠኮሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ 2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን ሠኮሩ ወረዳ መንገዶችና ሎጅስቲክስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ከልል ጅማ ዞን የሠኮሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ 2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
-
እስቴሽነሪ
-
የቢሮ ፈርኒቸር
-
የመኪና ፊልትሮ ፡ ዘይት እና ፍሬን ሸራ
-
የጽዳት ዕቃዎች
-
የሠራተኞች ደንብ ልብስ እና ጫማ
-
የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
-
የመኪና ጎማ
በዚሁ መሠረት-
-
ተጫራቾች ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ወይም የ 2017 ዓ.ም የመንግስት ግብር የከፈሉ እንዲሁም በአቅርቦት እና በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
-
ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ) ብር በመከፈል ሠኮሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር-5 በመቅረብ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለı5(አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት በመገኘት መግዛት ይችላሉ፡፡
-
ተወዳዳሪዎች ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ዕቃ ብር 10,000 (አሥር ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም (CPO) ከዋናው ቴክኒካል ሰነድ ጋር በአንድ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡
-
ንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 30/01/2018ዓ.ም እስከ 4፡00 ድረስ የእቃውን ዋጋ በመግለፅ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ Original & 2 Copy በወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
-
ጨረታው በ30/01/2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
-
እቃዎቹ በጥያቄያችን መሠረት ደረጃቸውን እና ጥራታቸውን የጠበቁ መሆን አለባቸው፡፡
-
ጨረታውን ያሸነፈ ድርጅት ዕቃዎቹን በጥራት ካላቀረበ ዕቃውን የማንቀበል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
-
ጨረታውን ያሸነፈ ድርጅት እቃውን እስከ ወረዳው ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
-
በመጨረሻ ወረዳው ወይም ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
ለለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር 0930504012 ወይም 0935152072 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን የሠኮሩ ወረዳ ገንዘብ ኢ/ት/ጽ/ቤት
