ቡና ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር ከዚህ በታች የተገለፁትን የህትመት አይነቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
BUNNA INSURANCE S.C (ቡና ኢንሹራንስ አ.ማ)
የጨረታ ማስታወቂያ
ቡና ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር ከዚህ በታች የተገለፁትን የህትመት አይነቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የህትመት ዓይነቶች
|
ተ.ቁ |
የእቃው ዝርዝር |
ብዛት |
የሎት ብዛት |
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን |
|
1 |
ዓመታዊ ሪፖርት መፅሔት |
350 ወይም 320 |
Lot (ጥቅል) 1 |
10,000 |
|
2 |
ፎልደር |
350 ወይም 200 |
በጨረታው ለመሳተፍ:-
- እያንዳንዱ ተጫራች ከላይ በጥቅል (Lot 1) ከተገለፁት የህትመት ዓይነቶች ዝርዝር ውስጥ በነጠላ ወይም በሁለቱም (Items) መወዳደር ይችላል።
- ተጫራቾች በመስኩ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሎቱ ከተገለፁት በአንዱም ሆነ በሁለቱ አይነት ህትመቶች ቢወዳደሩ ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) በኩባንያችን ስም በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ CPO) ብቻ አብረው ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ከተጠቀሰው መጠን በታች ያስያዘ ተጫራች ከጨረታ ውጭ የሚደረግ ይሆናል።
- ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ከአፍሪካ ሕብረት ጀርባ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ከፍ ብሎ በሚገኘው የቡና ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ ዋናው መ/ቤት ስለጨረታው የሚገልፀውን ሠነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ሁለተኛ ፎቆ ፋይናንስ የስራ ክፍል በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ግዥና ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል (ምድር ቤት) በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቬሎፕ ተደርጎ እስከ መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ በ4:30 ሰዓት በኩባንያው ዋና መ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ (ምድር ቤት) ይከፈታል።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-126-31-03 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
- ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡-
ቡና ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መ/ቤት
ግዥና ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል
የስልክ ቁጥር፡- 011-126-31-03
አዲስ አበባ
