Tender Detail

Tender Details

  • Company በገቢዎች ሚኒስቴር የጅማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
  • Address ጅማ ከተማ : ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 047-1-11-56-00
  • Website
  • Deadline07 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Securityየአገልግሎት ዋጋ 0.5% እስከ 2%
  • opening date2025-10-07 00:00:00
  • Categories Hotel Service Provision

በገቢዎች ሚኒስቴር የጅማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት አመት የሆቴሎች አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በገቢዎች ሚኒስቴር የጅማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር MOR JBO-001/2018

 

በገቢዎች ሚኒስቴር የጅማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት አመት የሆቴሎች አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በሆቴል ዘርፍ የተሰማራ በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው፤ የተ.እ.ታ ተመዝጋቢ የሆነ በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ወይም ከሚመለከተው አካል የተሰጠ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል ለጅማ ባለ ሶስት ኮከብ ደረጃ እና ከዛ በላይ ያለው ሲሆን ለአሶሳ፣ ጋምቤላ ፤ ሚዛን እና ነቀምት ታክስ ማዕከል የኮከብ ደረጃ መስፈርት ግዴታ አይደለም።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ጠቅላላ የሞላችሁትን የአገልግሎት ዋጋ 0.5% እስከ 2% በማስላት በባንክ ክፍያ ማስያዣ (C.P.O) ወይም በጥሬ ገንዘብ በገቢዎች ሚኒስቴር ጅማ ቅ/ጽ/ቤት ስም ማስያዝ የሚችል።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:00-6፡00 እና ከሰዓት 7፡00-11፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት በገቢዎች ሚኒስቴር ጅማ ቅ/ጽ/ቤት መርካቶ አዋሽ ባንክ ህንፃ 4ኛ ፎቅ ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. የአገልግሎት ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በጥንቃቄ በመሙላት በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ፊርማና የድርጅቱ ማህተም በመምታት በታሸገ ኤንቨሎፕ ቴክኒካሉን እና ፋይናንሽያሉን ዋናው እና ኮፒው ለየብቻ በኤንቨሎፕ ወይም ካኪ ፖስታ በማሸግ በቅ/ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚችሉ።
  6. ጨረታው የሚዘጋበትና የሚከፈትበት ሰዓት ከጨረታ ሰነድ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የጨረታ ሰነድ መቀየር፣ ማሻሻል ወይም ከጨረታው ራስን ማግለል አይቻልም፡፡
  8. የተሰረዘና የተደለዘ፣ የተፋፋቀ እንዲሁም በግልፅ የማይነበብ የጨረታ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም፤
  9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
  10. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 047-111-56-00/047-211-04-43 ደውለው መጠየ ይችላሉ።

 

በገቢዎች ሚኒስቴር የጅማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

 

Save Tender