በምሥራቅ ጉራጌ ዞን የመስቃን ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በካፒታልና በሥራ ማስኬጃ በጀት ለተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በምሥራቅ ጉራጌ ዞን የመስቃን ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በምሥራቅ ጉራጌ ዞን የመስቃን ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በካፒታልና በሥራ ማስኬጃ በጀት ለተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት 1. የስቴሽነሪ /የጽሕፈት መሣሪያ
ሎት 2. የሞተር ብስክሌት
ሎት 3. የሞተር መለዋወጫ ዕቃዎች
- ተጫራቾች ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የዕቃው አቅራቢነት ምዝገባ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር የያዘውን ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የዕቃዎቹን ስፔሲፊኬሽን በተገለጸው መሰረት ተሞልቶ እንዲገለጽና ለሎት 1 የማይመለስ 100 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት የመ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት በመቅረብ የተዘጋጀውን ሰነድ መግዛት የምትችሉ መሆኑን።
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ዋጋ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 /አስር ሺህ/ በባንክ በተመሰከረለት (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በተዘጋጁት ዝርዝር ስፔሲፊኬሽን ላይ ሞልተው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች /ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ ቀኑ ቅዳሜና አሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የተጫራቾች አለመኖር ፖስታው ተሟልቶ እስከተገኘ ድረስ ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉልም፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ዕቃውን የወረዳው ፋይናንስ ድረስ ማስረከብ ይጠበቅበታል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0461151102 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በምሥራቅ ጉራጌ ዞን የመስቃን ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
